መነሻ ገጽ ከ23 አመት በታች የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የማሊ አቻውን ዛሬ ይገጥማል
ከ23 አመት በታችዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የማሊ አቻውን ዛሬ ይገጥማል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ ከማሊ አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል።

ከቀኑ 10 ሰአት ላይ የሚካሄደው ጨዋታው በጃፓን ቶኪዮ እ.አ.አ በ2020 ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ እግር ኳስ ውድድር ለመሳተፍ የሚደረግ የማጣሪያ ጨዋታ ነው።
የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኑ በህዳር ወር 2011 ዓ.ም ባደረገው የአፍሪካ ዞን የኦሎምፒክ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሶማሊያ አቻውን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወሳል።
በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚሰለጥነው ብሔራዊ ቡድኑ ለጨዋታው ቅድመ ዝግጅት ይረዳው ዘንድ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሲሸልስ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርጎ 1 ለ 0 እና 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
ተጋጣሚው የማሊ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኑ ትናንት ማታ ከምሽቱ 4 ሰዓት አዲስ አበባ መግባቱ ታውቋል ።

ናምቢያዊው ጃክሳን ፓቫዛ ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።
የነገው ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ዋጋ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የስታዲየም መግቢያ ዋጋ እንደሆነም ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም በማሊ (ባማኮ) ላይ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች የኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን የማሊ አቻውን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በቀጣዩ ዙር ማጣሪያ ከሩዋንዳ፣ ሞሮኮና ዴሞክራቲክ ኮንጎ አንዳቸውን የሚያገኝ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ይህን ዙር ካለፈች ደግሞ በታህሳስ 2012 ዓ.ም በግብፅ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ አገሮች የኦሎምፒክ ውድድር የመሳተፍ አድል ይደረሳታል።
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ከወጣች ደግሞ ለቶኪዮ የእግር ኳስ ውድድር በቀጥታ አልፋ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሎምፒክ እግር ኳስ ውድድር ትሳተፋለች ማለት ነው።
ጃፓንን ጨምሮ 16 አገሮች በሚሳተፉበት የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ከአፍሪካ አህጉር በወንዶች እግር ኳስ ሶስት አገሮች ይወከላሉ።
እ.አ.አ በ2020 በጃፓን ርዕሰ መዲና ቶኪዮ በሚካሄደው የኦሎምፒክ ጨዋታ የእግር ኳስ ዘርፍ በአህጉራት ተከፋፍለው በሚደረጉ ከ23 ዓመት በታች ውድድሮች በሚመዘገቡ ውጤቶች መሰረት አገሮች ለውድድሩ የሚያልፉ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...