መነሻ ገጽ ዜናዎች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ  ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ ተራዘመ
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ  ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ ተራዘመ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ተራዘመ።
 ነገ ቅዳሜ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ ለአራተኛ ጊዜ መራዘሙ ታውቋል።

ምርጫዎ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ ለመወያየት የፊፋ ልዑክ መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣ ተገለጸ ።

የፌደሬሽኑ ጊዜያዊ ዋና ጸሐፊ  አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ለሀትሪክ ድህረ-ገጽ እንደገለጹት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽኖች ማህበር ፊፋ ረቡዕ ዕለት ለፌደሬሽኑ በላከው ደብዳቤ አማካኝነት ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ
አቶ ሰለሞን ገ/ስላሴ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባሳለፈነው ጥር ወር ምርጫው የሚካሄድበትን ቀን ለካፍና ለፊፋ አስቀድሞ ባለማሳወቁ ምክንያት ምርጫው ሊራዘም መቻሉ ፊፋ በላከው ደብዳቤ ማስታወቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንትና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ምርጫ በተረጋጋና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ማድረግ በሚቻልበት ዙሪያ ለመወያየት የፊፋ ልዑክ መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣም ጠቁመዋል።

የፊፋ ልዑክ በምርጫው ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ካደረገ በኋላ ምርጫው የሚካሄድበትን ቀን ይፋ እንደሚደረግ ነው አቶ ሰለሞን ያብራሩት።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...