መነሻ ገጽ ኢቢሲ አዋርድ የኢቢሲ ስፖርት ሽልማት መስከረም መጀመሪያ ይካሄዳል
ኢቢሲ አዋርድዜናዎች

የኢቢሲ ስፖርት ሽልማት መስከረም መጀመሪያ ይካሄዳል

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው “ኢቢሲ ስፖርት ሽልማት” ለሁለተኛ ጊዜ መስከረም 6 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ።

ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ በእግር ኳስ የዓመቱ ምርጥ ወንድና ሴት ተጫዋች፣ በአትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ ወንድና ሴት አትሌት እንዲሁም የሕይወት ዘመን ዘርፍ አምስት ስፖርተኞች ለሽልማት ይበቃሉ።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤል አዳሙ እንደገለጹት፤ ሽልማቱ በስፖርተኞች መካከል ጠንካራ የፉክክር ስሜት በመፍጠር አገሪቱን በዓለም አቀፍ መድረክ በስፖርቱ ውጤታማ ለማድረግ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ለሽልማቱ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት በ2010 በሁለቱም ፆታ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ውጤታማ እንቅስቃሴ ያደረጉ የእግር ኳስ ተጨዋቾች መሆናቸውን የኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዮናስ ተሾመ ገልጸዋል።

በሁለቱም ፆታ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት አስር ወንድና አስር ሴት እግር ኳስ ተጫዋቾች የተመረጡ ሲሆን በአትሌቲክስ ስፖርት በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ውድድሮች ውጤታማ ሆነው ያጠናቀቁ አምስት ወንድ እና አምስት ሴት አትሌቶች መመረጣቸውን ተናግረዋል።

ለሽልማት የቀረቡት እጩ ተወዳዳሪዎች 30 በመቶ ከስፖርት ቤተሰቡ በሚሰበሰብ ድምጽና 70 በመቶ በባለሙያዎች በሚሰጥ ነጥብ አሸናፊዎቹ እንደሚለዩ አቶ ዮናስ ገልጸዋል።

የድምጽ አሰጣጡ ለእጩዎች የሚሰጠውን መለያ ኮድ በ801 ላይ አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ፣ በኢቢሲ ማህበራዊ ሚዲያና ድረ ገጽ በመጠቀም እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

ለሽልማት የቀረቡት እጩ ተወዳዳሪ ስፖርተኞች በሚያገኙት ድምጽና ነጥብ መሠረት በየዘርፉ አሸናፊ የሆኑ ሦስት ስፖርተኞች መስከረም 6 ቀን 2011 በሸራተን አዲስ በሚካሄድ ሥነ ስርዓት ላይ ይለያሉ።

የዘንድሮው የኢቢሲ ስፖርት ሽልማት ልዩ የሚያደርገው የህይወት ዘመን የስፖርት ዘርፍ እንዲካተት በመደረጉ እንደሆነም ኮሚቴው አስታውቋል።

ወደፊት ሽልማቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ለመሸለም ዕቅድ መኖሩም ተጠቅሷል።

ባለፈው ዓመት በተካሄደው የኢቢሲ ስፖርት ሽልማት የዓመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች በወንድ አስቻለው ታመነ በሴቶች ደግሞ ሎዛ አበራ አሸናፊ ነበሩ።

እንዲሁም በአትሌቲክስ የዓመቱ ምርጥ አትሌት በወንድ ሙክታር እንድሪስ በሴት አልማዝ አያና አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል።

እያንዳንዳቸውም የዋንጫ፣ የምስክር ወረቀትና የ75 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዘንድሮው ውድድር ላይ በእጩነት የቀረቡት በወንዶች እግር ኳስ ከጅማ አባጅፋር ተመስገን ገብረ ኪዳን፣ ይሁን እንዳሻው፣ ሔኖክ አዱኛ፣ ከአዳማ ከነማ ከነዓን ማርክነህ፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አብዱልከሪም መሐመድና ሙሉዓለም መስፍን፣ ከኢትዮጵያ ቡና አማኑኤል ዮሐንስ፣ ከመከላከያ ምንይሉ ወንድሙ፣ ከመቐለ ከተማ አማኑኤል ገብረሚካኤል እንዲሁም ከሲዳማ ቡና አዲስ ግደይ ናቸው።

በሴቶች እግር ኳስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ መሰሉ አበራ፣ ከሐዋሳ ከተማ ምርቃት ፈለቀ፣ ከደደቢት ሎዛ አበራ፣ ብርቱካን ገብረ ክርስቶስና ሰናይት ቦጋለ፣ ከንግድ ባንክ ህይወት ደንጊሶ፣ ከአዳማ ከነማ ሴናፍ ዋቁማ፣ ከመከላከያ እመቤት አዲሱ፣ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ አለምነሽ ገረመው እና ከኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ አረጋሽ ካልሳ ተመርጠዋል።

በተመሳሳይ በሴቶች አትሌቲክስ ከሙገር ሲሚንቶ ገንዘቤ ዲባባ፣ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀብታም ዓለሙ፣ ከኦሮሚያ ውሃ ስራዎች ዮሚፍ ቀጄልቻና ነጻነት ጉደታ፣ ከንግድ ባንክ አርያት ዲቦ እና ከጉና ንግድ ግርማዊት ገብረ እግዚያአብሔር ሲሆኑ በወንዶች ከደቡብ ፖሊስ ሰለሞን ባረጋ፣ ከመከላከያ ጌታነህ ሞላ፣ ከኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሳሙኤል ተፈራ እና ከአማራ ማረሚያ ቤቶች ጀማል ይመር ተመርጠዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...