የስሑል ሽረ ስታዲዮም ከፌደሬሽኑ በተላኩ አባላት ተገምግሟል

ለመወዳደሪያ ብቁ አይደለም ተብሎ እድሳት ላይ የነበረው ስታዲዮሙ ዛሬ ከፌደሬሽን በተላኩ ሰዎች ተገምግሟል።

ገምጋሚዎቹ በሚያቀርቡት ሪፖርት በቀጣይ ቀናት የስታዲዮሙ እጣፈንታ የሚለይለት ሲሆን በአሁኑ ስአት በሽረ ስታዲዮም በመገኘት ከፌደሬሽኑ የተላኩ ገምጋሚዎች ተጎብኝቷል። በዘንድሮው አመት ስሑል ሽረዎች የመጀመሪያውን ዙር በትግራይ ስታዲዮም ሲያከናውኑ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን ሜዳው በፌደሬሽን ፍቃድ ካገኘ ወደ ሜዳቸው በመመለስ ውድድራቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer