መነሻ ገጽ አፍሪካ  ዜና ኮንፌዴሬሽን ካኘ | ዚማሞቶ ኢትዮጵያ ከደረሰ 3ኛ ልምምዱን ዛሬ ሰርቷል።
አፍሪካወላይታ ድቻዜናዎች

 ዜና ኮንፌዴሬሽን ካኘ | ዚማሞቶ ኢትዮጵያ ከደረሰ 3ኛ ልምምዱን ዛሬ ሰርቷል።

አጋራ
አጋራ

በአፍሪካ የክለቦች የኮንፌድሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ የሆነው የወላይታ ዲቻ  ተጋጣሚ የሆነው የዛንዚባሩ ዚማሞቶ ነገ(ረቡዕ) በ10 ሰአት ላለበት የመልስ ጨዋታው ዛሬ 3ኛ ልምምዱን አከናውኗል።
በአሰልጣኝ ሞሱማ አብዱላሂ የሚመራው የዛንዚባሩ ቡድን ዚማሞቶ እንደ ወላይታ ድቻ ሁሉ ዘንድሮ የአፍሪካ የክለቦች ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ የመጀመሪያው ሲሆን በዘንድሮው የዛንዚባር ሊግ ደግሞ 14ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት አጠናቋል።

አሰልጣኝ ሞሱማ አብዱላሂ በሰጡት አስተያየት “በመጀመሪያው ጨዋታ እንቅስቃሴ በጣም በልጠናቸው ነበር፤ ወደ 4የሚጠጉ ግልፅ ኳሶችን አምክነናል። በሁለተኛው አጋማሽ ግን ተጋጣሚያችን ወላይታ ድቻ በጥብቅ የመከላከል ብቃት ስለተጫወቱ ግብ ለማግባት ተቸግረናል።” በማለት ተናግረዋል።

 ስለ ነገው ጨዋታም የተጠየቁት አሰልጣኙ “እዚህ የመጣነው የሚቻለንን ሁሉ ለማድረግ ነው፤ ወላይታ ድቻ ከኛ የተሻለ እድል አላቸው፤ ከሜዳቸው ውጪ ጎል ማስቆጠራቸው በትልቅነቱ ይጠቅማቸዋል። ስለዚህ ከማራጭ ስለሌለን ከባድ ፍልሚያ አድርገን ግብ ለማስቆጠር ወደ ሜዳ እንገባለን።” ሲሉ የቀድሞው የዛንዚባር ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። 

ጨዋታው ነገ(ረቡዕ) ልክ 10:00 ሲል በሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...