መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዜና | በካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ወላይታ ድቻ እና ቅ/ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸው ታወቁ።
ቅዱስ ጊዮርጊስአፍሪካካፍኮንፌድሬሽን ካፕወላይታ ድቻዜናዎች

ዜና | በካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ወላይታ ድቻ እና ቅ/ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸው ታወቁ።

አጋራ
አጋራ

በካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ተሳታፊ የሚሆኑት ኢትዮጵያን የወከሉት ወላይታ ድቻ እና ቅ/ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸው ታወቁ። በዚህም መሰረት ወላይታ ድቻ ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካ ጋር የተደለደለ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ በአንፃሩ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎውን ካራ ብራዛቪልን የሚገጥም ይሆናል።

ወላይታ ድቻ ለዚህ ውድድር የበቃው በአንደኛው ዙር የግብፁን ሀያል ክለብ ዛማሌክን በደርሶ መልስ ውጤት በማሸነፍ ሲሆን ቅ/ጊዮርጊስ በበኩሉ በሻምፒዮንስ ሊጉ በዩጋንዳው ኬሲሲኤ በድምር ውጤት 1-0 ተሸንፎ በመውደቁ ወደ ምድብ ድልድሉ መግባት ሳይችል ቀርቶ ለዚህ ውድድር ደርሷል።

ወላይታ ድቻ የመጀመሪያውን ጨዋታ ወደ ታንዛኒያ ተጉዞ ከመጋቢት 28-30 (እ.ኤ.አ ሚያዝያ 6-8) ባሉት ቀናት የሚያከናውን ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ከ10 ቀናት በኋላ ከሚያዚያ9-10 ( እ.ኤ.አ ሚያዝያ 17-18) ሀዋሳ ላይ የሚደረግ ይሆናል። ቅ/ጊዮርጊስ ደግሞ የመጀመሪያ ጨዋታውን አ/አ ላይ በተመሳሳይ ቀን የሚያደርግ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ወደ ኮንጎ አምርቶ የሚያከናውን ይሆናል።

ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታዎቻቸውን የሚያሸንፉ እና የሚያልፉ ከሆነ 16 ቡድኖች ወደሚሳተፉበት የምድብ ድልድል መቀላቀል ይችላሉ። የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ሙሉ ጨዋታዎች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...