መነሻ ገጽ ሪፖርት ​ሪፖርት | ወልዋሎ አዲግራት በአቻ ውጤት የመጓዙን መንገድ ቀጥሎበታል
ሪፖርትሲዳማ ቡናወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

​ሪፖርት | ወልዋሎ አዲግራት በአቻ ውጤት የመጓዙን መንገድ ቀጥሎበታል

አጋራ
አጋራ

በሶስተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡናን ያስተናገደው ወልዋሎ አዲግራት.ዮ  ለሶስተኛ ግዜ በአቻ ውጤት ጨዋታውን አጠናቋል፡፡
ልክ 9ሰዓት ሲል የጀመረው ጨዋታ እንደተለመደው የወልዋሎ አዲግራት ሜዳ በደጋፊዎቻቸው አስደናቂ ድባብ የታጀበ  ነበር ፡፡

በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ግዜ አረንጓዴ ማሊያ የለበሱት  ሲዳማ ቡናዎች  ከፍፁም ተፈሪ በሚላኩ ኳሶች በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ የተሻሉ ነበሩ፡፡

በ34 ደቂቃ ላይ የወልዋሎን የተከላካይ ክፍል ሲያስጨንቅ የነበረው ባይ ገዛኸኝ የወልዋሎ ተከላካይ ከኤፍሬም ጌታቸውን በመንጠቅ ያስቆጠራት ጎል የጨዋታው የመሀል ዳኛ አዳነ ወርቁ ጥፋት ተሰርቷል በሚል ልትሻር ችላለች፡፡
ከእረፍት መልስ ወልዋሎዋች ብርሀኑ አሻሞን በአፍወርቅ ሀይሉ ቀይረው ወደ ወደጨዋታው ለመመልስ ሙከራ ቢያደርጉም የሲዳማ ቡናን የመሀል ክፍል ሰብረው ለመግባት አልቻሉም፡፡

በ65ኛ ደቂቃ ላይ ወልዋሎ አዲግራት  ሁለት የተጫዋቾች ቅያሪ ሲያደርጉ ከደር ሳሊህን በኘሪንስ ሰርቪንሆ እንዲሁም አብዱራህማን ፋይሴንን በ እለቱ ጥሩ ያለነበረውን መኩሪያ ደሱን ቀይረው አስገብተዋል፡፡ በእለቱ እንብዛም የጎል ሙከራ ያለተደረገበት የወልዋሎ ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ሁለት ለጎል የቀረቡ ኳሶችን ሲያድን በተለየ  የተከላካይ መስመር ተጨዋቹ ኤፍሬም ጌታቸው የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ አዲስ ግደይ የሞከረውን ኳስ የወልዋሎ ተከላካዮች ተረባርበው ጎል ከመሆን ያዳኗት ኳስ ተጠቃሽ ነበረች::ባጠቃላይ ጨዋታው ግጭት የበዛበት የነበረ ነገር ግን 1የቢጫ ካርድ የታየበት የነበረ ሲሆን ጨዋታው ያለምንም ጎል 0-0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ሲዳማ ቡናዎችም አዲግራት ለመድረስ 1181 km በመጓዝ አንድ ነጥብ ይዘው ወደ ይርጋለም መመለስ ችለዋል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...