በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ወላይታ ድቻን በመልቀቅ ለአዲስ አዳጊዎቹ መቐለ ከተማዎች ፊረማውን ያኖረው ዮሴፍ ደንገቶ ከሳምንታት በፊት በስምምነት መለያየቱ እሚታወስ ነው።
ዮሴፍ ከመቐለ ከተማ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቷል። ይህንን ተከትሎ የተጫዋቹ ፈላጊ ሆኖ የተገኘው በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ እሚመራው ጅማ አባጅፋር ማረፊያው መሆኑ ተሰምቷል ።
ጅማ አባጅፋር ተጨዋቾችን ለአንድ አመት እንደሚያስፈርመውም ታውቋል።ተጫዋቾቹ አዲሱ ቡድኑንን በተመለከተ እና ከመቐለ ከተማ ገር የተለያዩበትን ሆኔታ ለድህረ ገጻችን ሀትሪክ ስፖርት ሲናገር።
“ከመቐለ ከተማ ጋር የተለያየሁት በስምምነት ነው። ከጅማ አባጅፋር ጋር በቃል ደረጃ ተስማምተናል ባሳለፍነው ሳምንት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ሰርቻለሁ። በቀጣዩ ረቡዕ ወደ ካንፕ በመግባት ትሬኒንግ እንጀምራለን። በአሁኑ ሰዓት ለእረፍት ሶዶ ነው የምገኘው በቀጣዮች ቀናት የወረቀት ስራዎች ይጠናቀቃሉ።ከጅማ አባጅፋር ጋር መልካም የውድድር ግዜ ይኖረናል ብይ ተስፋ አደርጋለሁ።”
ዮሴፍ ደንገቶ ከዚህ ቀደም ለመታህራ ስኳር( በብሔራዊ ሊግ) ለወላይታ ድቻ ለአምስት አመታትን ተጫውቶ ሲያሳልፍ ከአዲስ አዳጊው መቐለ ከተማ ጋር ግማሽ ዓመት ቆይታን ማድረጉ እሚታወስ ነው።
አስተያየት ይስጡ