በድሬዳዋ ተወልዶ እስከ የመን ድረስ በደረሰው የኘሮፌሽናል ህይወቱ ከድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ ፤ መብራት ሀይል፤ኢትዮጵያ ቡና ፤ በየመኑ አልሳክር አናለኢትዮጵያ ታዳጊ እና ወጣት ብሔራዊ ቡድን በመጫወት ደማቅ ታሪክን ማፃፍ ችሏል፡፡ በ1993 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ውድድር በ26 ጨዋታዎች 24 ጎሎችን በማስቆጠር ለ16 ዓመታት ሪከርዱን በመያዝ ለብዙ ኢትዮጵያን ወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች እንደ ተምሳሌት የታየ እግርኳሰኛ ነበር፡፡
በዛሬው እለት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ከእግር ኳስ በክብር እሚሸኝበትን ኘሮግራም ለሚዲያዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በመወከል እውቅና በመስጠት ንግግር ያደረጉት አቶ ሰለሞን ገብረስላሴ ግዚያዊ ዋና ፀሀፊ እንዲሁም የውድድርና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ በንግግራቸው :-“በመጀመሪያ ተወዳጁ የእግርኳስ ተጫዋቾች ዮርዳኖስ አባይ ለዚህ ቀን ስለደረስክ እንኳን ደስ አለህ ማለት እፈልጋለሁ፡፡በኢትዮጵያ እግርኳስ ውስጥ ሊከበሩ እሚገባቸው ተጫዋቾች ናቸው፡፡
ከተለያዩ ቦታዎች በመምጣት ለክለባቸው እና ለብሔራዊ ቡድን ግልጋሎታቸውን ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ አካላት ከእግርኳሱ ሲሸኙ አላማ አለው ከታች ለሚመጡ ወጣቶች አርአያ ይሆናሉ፡፡በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ና በእግር ኳስተመልካቾችም ዘንደ ዮርዳኖስ አባይ ትልቅ እውቅና አለው፡፡ይህ ተጫዋቾች እንደዚህ አይነት ፕሮግራም በሚያዘጋጅበት ወቅት የእግርኳስ ፌዴሬሽኑ የበኩሉን ትልቅ ድጋፍ ማድረግ አለበት፡፡እንደምታውቁት በአንድ እስታዲየም በጣም በተጣበበ ፕሮግራም እንደምናካሄድ ይታወቃል፡፡ነገር ግን ይህ መሠረታዊ እና ድጋፍ ማድረግ ስላለብን የአንድ ቀን ፍቃድ ሰጠነው ሁለት በሚወዳቸው ቡድኖች መካከል በኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና በኢትዮጵያ ቡና መካከል እሚደረገውን ጨዋታ የተለያዩ ቴክኒካዊ ድጋፎችን እንደምናደርግለት ቃለ በመግባት ለዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ቀን ደርሰናል፡፡”በማለት ንግግራቸውን ቋጭተዋል፡፡
በመቀጠል ንግግር ያደረገው
የፕሮግራሙ ባለቤት ዮርዳኖስ አባይ ሲሆን
“በመጀመሪያ የሚዲያ አካላትን ማመስግን እፈልጋለሁ፡፡ በእግር ኳስ በቆየሁባቸው ግዚያት አብረውኝ የተጫወቱ ተጫዋቾች ያሰልጠኑኝ አሰልጣኞች ትልቅ ቦታና ምስጋና አለኝ ፡፡ የሽኝቱ ፕሮግራም የኔ ብቻ እንዲሆን አልፈልግም ማስተማር እንፈልጋለን፡፡ ከኔ በፊት አሸነፊ ግርማ መፀሀፍ አሳትሟል እንዲሁም ሙልጌታ ምህረትም ሀዋሳ ላይ በክብር ተሸኝተው አልፈዋል፡፡ ከኔም በኃላ ያሉ ልጆች በክብር እንዲሸኙ እንደ ምሳሌ መሆንና ቀጣይነት እንዲኖረው እንፈልጋለን፡፡

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ከኛ በፊት ያለፉት እና ወደፊት ለሚመጡት ክብር መስጠት አለብን፡፡ታላላቆቻችንን ብቻ ሳይሆን ታናናሾቻችንም ማክበር አለብን፡፡ ያዘጋጀነው ፕሮግራም ላይ ከተሳካልን ድሬዳዋ ላይ እሩጫ ለማካሄድ አስበናል፡፡አንዲሁም ወጣቶች እንዲማሩበት ዶክመንተሪ ፊልም አዘጋጅተናል፡፡ የኔ ሽኝት ሆኖ ብቻ እንዲያልፍ አልፈልግም፡፡ በተለይ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ በጣም በአስደንጋጭ ሁኔታ የኩላሊት ህመምተኞች አሉ እነሱን በመረዳት በበጎ አድራጎት ላይ መሳተፍ እንፈልጋለን፡፡በዚህ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ድርጅቶች አግዘውናል፡፡ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ከልብ ማመስገን አፈልጋለሁ፡፡ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ እና የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለቦች ይሄ ፕሮግራም እንዲሳካ አግዘውናል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በተለየዩ ነገሮች ድጋፍ አያደረጉልን ይገኛሉ፡፡እነሱንም ማመስገን እንፈልጋለን፡፡”በማለት ስለፕሮግራሙ ማብራራያ መስጠት ችሏል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ የኩላሊት እጥበት ህሙማን አገለግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን አሰፋ በበኩላቸው ለተጫዋቾቹ ያለቸውን አድናቆት በመግለፅ ለኩላሊት ህመምተኞች የተለያዩ የድርሻ አካለት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡ በኘሮግራሙ ከሚዲያ አካለት ስለ ዶክመንተሪ ፊልሙ ለቀረበለት ጥያቄ ፊልሙ የ1ሰዓት ከ15 ደቂቃ መሆኑን በመግለፅ ከድሮ ጀምሮ በምስራቀለ ክልል የነበሩ ተጫዋቾችን ጨምሮ ያለውን ሂደት ለማስቀኘት መሞከሩን ና የተሳካ ስራ መሰራቱን ተገልጿል፡፡ ፊልሙን በድምፅ በኩል በመተረክ ጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

በመጨረሻም የኢትዮ ኤሌክትሪክ ቀንደኛ ደጋፊ በመሆን እሚታወቁት በቀለ ኮረንቲ ለተጫዋቾቹ ያላቸውን አድናቆትና ፍቅር በመግለፅ ለተጫዋቾቹ ያዘጋጅትን ስጧታ በማበርከት ጋዜጣዊ መግለጫው ፍፃሜውን አጊንቷል፡፡

አስተያየት ይስጡ