መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ ቡና ጸጋዘአብ አስገዶምን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አድርጎ ለመቅጠር ተስማማ
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ጸጋዘአብ አስገዶምን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አድርጎ ለመቅጠር ተስማማ

አጋራ
አጋራ

ከግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ውብሸት ጋር በስምምነት የተለያየው ኢትዮጵያ ቡና የቀድሞው የደደቢት ግብ ጠባቂና እስከተጠናቀቀው የውድድር ዓመት መጨረሻ ደግሞ የግብ ጠባቂ አሰልጠኝ የነበረውን ጸጋዘአብ አስገዶምን የክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ አድርጎ ለመቅጠር መስማማቱን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ የሀትሪክ ስፖርት ምንጮች ገለጹ፡፡
የክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ውብሸት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ተመርጦ ለዝግጅት ሓዋሳ የሚገኝ ሲሆን የክለቡን ኃላፊነት ከብሔራዊ ቡድን ኃላፊነት ጋር ደርቦ መስራቱ በክለቡ ቅድመ- ውድድር ዝግጅት ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ተብሎ ስለታመነበት ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ጠዋት ለቅድመ-ውድድር ዝግጅት ወደባህር ዳር የሚሄድ ሲሆን አዲሱ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ጸጋዘአብ አብሮ ከክለቡ እንደሚጓዝ ታውቋል፡፡
በተያያዘ ዜና ለክለቡ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዳሮሳ ጎሜስ ረዳት በመፈለግ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና በመጪው ሳምንት መጀመሪያ ላይ አዲስ ረዳት አሰልጣኝ ክለቡን እንደሚቀላቀል ለማውቅ ተችሏል፡፡ ከቀድሞ ረዳት አሰልጣኞች ጋር በስምምነት የተለያየው ክለቡ የተለያዩ አሰልጣኞች እያናገረ ሲሆን በፍጥነት ቅጥሩ ተጠናቆ አዲሱ ረዳት አሰልጣኝ የቡድኑን ዝግጅት ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...