መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና አዞዎቹን በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀምሯል 
ሪፖርትአርባምንጭ ከተማኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና አዞዎቹን በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀምሯል 

አጋራ
አጋራ

​በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 4ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛ ድሉን ውጥረት ውስጥ የሚገኘውን የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማርያምን አርባምንጭ ከተማ 2-0  በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀመሯል፡፡

በአዲሰአበባ ስታዲየም 11:30 ሲል የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በደጋፊዎቻቸው ድባብ የታጀበ ነበር፡፡ 

በመጀመሪያው አጋማሽ  ባለሜዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናዎች ተጭነው ወደ ጎል በመደረስ  የተሻሉ ነበሩ፡፡ አርባምንጭ ከተማ በታራኒው ሀይል ላይ የተመረኮዘ ጨወታን በመጫወት  በተደጋጋሚ ጥፋት ሲፈፅሙ ተስተውለዋል፡፡ በጨዋታው የመጀመሪያ የጎል ሙከራ በ18 ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳኑሚ ግልፅ የማግባት አጋጣሚውን ሳይጠቀምበት ሲቀር በእለቱ ጥሩ የነበረው ሳምሶን ጥላሁን እንዲሁም ኤሊያስ ማሞ ከ16.50 ውጪ ያደረጉዋቸው የጎል ሙከራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡


በ27  ደቂቃ አዞዎቹ  ጎል ቢያስቆጥሩም ከጨዋታ ውጪ አቋቋም ላይ በመሆናቸው ጎሉ ሳይፀድቅ ቀርቷል፡፡ከ 4 ደቂቃዎች በኃላ ሳምሶን ጥላሁን መሀል ለ መሀል ለሳኑሚ የሰነጠቀለትን ኳስ ሳኑሚ በፑንት ወጋ ያደረጋት ኳስ ሲሳይ ባንጫ ቢመልሳትም በጥሩ አቋቋም ላይ የነበሰው በረከት ይሀሳቅ አጊንቶ ከመረብ አዋህዷታል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ የደቂቃዎች እድሜ ሲቀሩት ሳሙኤል ሳኑሚ ሁለተኛ ጎል እሚያስቆጥርበት አጋጣሚ ተጠፈጥሮ የጎል ብረት ሊመልስበት ችሏል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመሪያው ሁሉ አርባምንጭ ከተማ የአማካያቸው አማኑኤል ጎበና እንዲሁም የአጥቂ መስመር ተጫዋቻቸው ላኪ ሰኒ አለመኖር  በመሀል ክፍሉ ላይ ኳስ የማደራጀት እና የተስተካከሉ ኳሶችን ለአጥቂ የማድረስ እና ያገኙትን እድል አለመጠቀም  ጉልህ ችግር በጨዋታው እሚጠቀስ ነው፡፡  በ71 ኛ  ደቂቃ ላይ ሳሙኤል ሳኑሚ በግራ መስመር የዞ የገባውን ኳስ መሬት ለመሬት ያሻገረውን ኳስ የአርባምንጩ ተከላካይ አሌክስ አሙዙ በራሱ መረብ ላይ በማሳረፍ ኢትዮጵያ ቡና 2-0 እንዲመራ አስችሎታል፡፡ በዚሁ
ጨዋታው በባለሜዳው ኢትዮጵያ ቡና 2-0  አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡናም 1 ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ3 ጨዋታዎች ሁለቱን በማሸነፍ እና አንድ አቻ ተለያይቶ ሊጉን በ7 ነጥብ መምራት ጀምሯል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት 

 

ኮስታዲን ፓፒች-ኢትዮጵያ ቡና

-ቡድኔ ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ ነው በቀጣይም ከዚህ የተሻልን ሆነን እንቀርባለን፡፡

-በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድኔ ዓመቱን እንዲጫወት እምፈልገውን አቋም ነው ያሳዩት ተጫዋቾቼ፡፡

ፀጋዬ ኪዳነማሪያም -አርባምንጭ ከተማ

 

– ባለፈው ከተጫወትናቸው ጨዋታው ዛሬ የተሻለን ነበርን፡ የቡድኔ ወሳኝ ተጨዋቾች ላኪ ሰኒ እና አማኑኤል ጎበና በጉዳት ምክኒያት ባለመኖራቸው ከታዳጊ ቡድን ሦስት ልጆችን ለማምጣት ተገደናል፡፡

-በዳኝነቱ በኩል ምንም ቅሬታ የለኝም ፍትሀዊ ነበር

-ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ልዩ ድባብ ታግዞ 3ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...