መነሻ ገጽ ሪፖርት ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ወደ አሸናፊነት መምጣት አልቻለም
ሪፖርትኢትዮጵያ ቡናዜናዎችጅማ አባጅፋር

ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ወደ አሸናፊነት መምጣት አልቻለም

አጋራ
አጋራ

 

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት የመጨረሻ አንድ ጨዋታ ዛሬ ተደርጓል። በጨዋታውም ኢትዮጵያ ቡና ጅማ አባጅፋርን አስተናግዶ ያለግብ አቻ ሊለያይ ችሏል።

እንደ ቀድሞ በደጋፊዎች መሙላት ሳይችል የተከናወነው ይህ ጨዋታ ግቦች ሳይታዩበት 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። አዲሱ የዋጋ ጭማሪ ከሜዳ ብዙ ደጋፊዎችን እያሸሸ እንደሆነ የዛሬው እና የትናንቱ የሸገር ክለቦችጨዋታ  ማሳያ መሆን ይችላል። በተለምዶ ዳፍ ትራክ እና ካታንጋ ተብለው የሚታወቁት ቦታዎች ባዶ ሆነው ታይተዋል።

ሁለቱም ቡድኖች የውድድር አመቱን የመጀመሪያ 3ነጥብ ለማግኘት ያደረጉት ጨዋታ እንደመሆኑ ማራኪ ጨዋታ ይታይበታል ተብሎ በደጋፊው ቢጠበቅም ጨዋታው ግን አልፎ አልፎ ከሚታዩ ሙከራዎች በስተቀር ይህ ነው የሚባል ጨዋታ አልነበረም። ባለሜዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናዎች 5ኛው ደቂቃ ላይ በአጥቂው አቡበከር ናስር የሞከሩት ኳስ ወደ ውጭ ወጥቷል። በተደጋጋሚ ኳስ መነጣጠቅ የታየበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ኳስ ይዞ ለመጫወት ጅማ አባጅፋር ደግሞ ረጃጅም ኳሶችን ለመጠቀም ሲጥሩ ተስተውለዋል። ​​​​​​‍22ኛው ደቂቃ ላይ የጅማ አባጅፋሩ ኤርሚያስ ጥሩ ኳስ አግኝቶ ቢሞክርም ለጥቂት ወደ ውጭ ወጥቶበታል። 33ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው አስራት ቱንጆ መሬት ለመሬት የሞከረው ኳስ ለጎል የቀረበ ነበር። ከዚህ ሙከራ በኋላም አማኑኤል ዮሐንስ የሞከረው ኳስ የግቡ ቋሚ መልሶበታል። ከዚህች ሙከራ በኋላ ኢትዮጵያ ቡና በተደጋጋሚ ወደ ጅማ አባጅፋር የግብ ክልል መድረስ ቢችሉም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

ሁለተኛው አጋማሽ ላይም ኢትዮጵያ ቡና ኳሱን ተቆጣጥሮ ለመጫወት ሲሞክር ጅማ አባጅፋር በአንፃሩ ወደኋላ በማፈግፈግ አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት ወደ ቡና የግብ ክልል ለመድረስ ቢሞክሩም የተገኙትን አጋጣሚዎች መጠቀም አልቻሉም። በሁለተኛው አጋማሽ ደጋፊውን የሚያዝናና እና ይህ ነው የሚባል ምንም አይነት ሙከራ ሳይደረግበት መጠናቀቅ ችሏል። ውጤቱንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ነጥብ ሲያገኝ ጅማ አባጅፋር ደግሞ ሁለተኛ ተከታታይ ጨዋታ አቻ ወጥቷል። በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ቡና በ1ነጥብ እና በ1 የግብ እዳ 13ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ጅማ አባጅፋር ከኢትዮጵያ ቡና በ1ነጥብ ከፍ ብሎ በ2ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ሊጉን ሁለቱንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለውና በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ወልዋሎ አ.ዩ. በ6 ነጥብ እና በ3 ንጹሕ ግብ መሪነቱን ሲይዝ ፋሲል ከነማ፣ ሐዋሳ ከተማ፣ ባህርዳር ከተማ፣ አዳማ ከተማ እና ቅ/ጊዮርጊስ በእኩል 4ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። ወልቂጤ ከተማ፣ ሰበታ ከተማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያለምንም ነጥብ ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የፋሲል ከተማው ሙጂብ ቃሲም እና የወልዋሎ አ.ዩ. ሰመረ ሐፍተይ በእኩል 3ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሲመሩ ሽመክት ጉግሳ፣ ካርሎስ ዳምጠው፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ አዲስ ግደይ እና ዲዲየር ሊብሬ በእኩል 2ግቦች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ዋልያዎቹ በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታን ሊያደርጉ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ ሊያመራ ነው ነገር ግን የወቅቱ የብሔራዊ ቡድኑ...