ኢትዮጵያ ቡና ዘንድሮ አሰልጣኝ ፖፓዲች ክለቡን በክረምት ዝግጅት እና በደቡብ ካስትል ዋንጫ ላይ ከመሩ በኃላ ከአዲስ ከተማ ዋንጫ ጀምሮ በህመም ምክንያት ክለቡን ከለቀቁ በኃላ ሌላኛውን ሰርቪያዊ አሰልጣኝ ኮስታዲን ፓፒችን ወደ ክለቡ በማምጣት አስፈርመው ነበር፡፡አሰልጣኙ ክለቡን ይዘው እያሰለጠኑ ቆይታ በማድረግ ሦስት ጨዋታዎችን የመሩ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ግን የቤተሰብ ችግር አለብኝ ወደ ሀገሬ ሄጄ እመለሳለሁ በሚል ነበር ከሀገር መውጣት የቻሉት አሁን ግን ከወደ ደቡብ አፍሪካ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ከሆነ አሰልጣኙ ለደቡብ አፍሪካው የቀድሞ ክለባቸው ሮያል ኤግል ፊርማቸውን አኑረዋል ተብሏል፡፡ በተለይ ለክለቡ ቅርበት ያላቸው የደቡብ አፍሪካ ድህረ ገፆች አሰልጣኙ በውጤት ቀውስ ውስጥ፡ለሚገኘው ሮያል ኤግልስ መፈረማቸው አስታውቀዋል ፡፡

አሰልጣኙ በሮያል ኤግልስ ከዚህ ቀደም በነበራቸው ውጤት ታይቶ በትናንትናው እለት ሰኞ ፊርማቸውን ለክለቡ ያኖሩት፡፡ አሰልጣኙ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የውል ኮንትራት እያላቸው አሰልጣኙ በዚህ አይነት አወዛጋቢ ድርጊት ላይ መፈረማቸው ተቃውሞን ያስነሳ ሲሆን በቀጣይም ክለቡ ለ CAF ደብዳቤ እንደሚልክ ታውቋል፡፡
አስተያየት ይስጡ