አስተያየት| ወልቂጤ ከተማ 0-1 ሲዳማ ቡና

👉👉ሜዳው የሚያስገድደውን አድርገናል ዘርዓ ሙሉ (ሲዳማ ቡና)

👉👉 ያገኘናቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀማችን በዛሬው ጨዋታ ዋጋ አስከፍሎናል ደጋአረግ ይገዙ (ወልቂጤ ከተማ)

 

14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሁለት ቀሪ ጨዋታዎች ዛሬ ፍፃሚያቸውን ሲያገኙ ወልቂጤ ወልቂጤ ከተማ ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ 1-0 ከተሸነፉ በኋላ የሁለቱም ቡድን አሰልጣኞች አስተየያታቸውን ሰጥተዋል።

ሜዳው የሚያስገድደውን አድርገናል ዘርዓ ሙሉ (ሲዳማ ቡና)

ስለጨዋታው

ሜዳው የሚያስገድደውን አድርገናል። ኳስ ይዞ ለመጫወት ምቹ ስላልሆነ ስለዚህ ያለው አማራጭ ዛሬ የተጫወትነው አጨዋወት ከአጨዋወታችን ውጪ ነው። ኳሶን ከሜዳችን ቶሎ ቶሎ ማውጣት። ያገኘነውን አጋጣሚ ግብ ማድረግ ነበር ደግሞም ተሳክቶልናል። እናም በተጫዋቾቼ በጣም ኮርቻለው ምክንያቱም በታክቲካል ዲሲፕሊን ሙሉ 90 ደቂቃ ጥሩ ነበሩ። እነሱ ሜዳውን ስለሚያውቁት በሚገባ ረጃጅም ኳሶችን ነው ሚጫወቱት። እሱን ተቆጣጥረን የነሱን ተጫዋቾች ስላቆምናቸው ውጤት ይዘን እንድንወጣ አግዞናል።


ያገኘናቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀማችን በዛሬው ጨዋታ ዋጋ አስከፍሎናል ደጋአረግ ይገዙ (ወልቂጤ ከተማ)

ስለጨዋታ

ጨዋታው እንዳያችሁት ነው። ባሰብነው መንገድ መከወን አልቻልንም። በተለይ የመጀመሪያው 45 ተጫዋቾቼ ጨዋታውን አሸንፈው ለመውጣት ከፍተኛ ጉጉት ውስጥ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ቀስ ብሎ ወደ ፊት ለመንቀሳቀስ ተቸግረን ነበር። ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ግን ከመጀመሪያው አጋማሽ የተለየ እንደነበር አንተም የተመለከትከው ነው። ያገኘናቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀማችን በዛሬው ጨዋታ ዋጋ አስከፍሎናል። እነሱ አንድ ድል ፈጥረው በሚገባ ተጠቅመው አሸንፈዋል እኛ ደግሞ ነጥብ አጥተናል።