አስተያየት| ኢትዮጵያ ቡና 1-1 ወልቂጤ ከተማ

👉👉 “ስትራቴጂ መቀየር ካስፈለገ ኳስ ተጫዋች መለወጥ ያስፈልጋል” (ካሳዩ አራጌ ኢትዮጵያ ቡና)

👉👉 ለጨዋታው ይዘነው የገባነው አጨዋወት ተጫዋቾቼ ለመተግበር የሚችሉትን ያህል ጥረት አድርገዋል (ደግአረግ ይግዛው ወልቂጤ ከተማ)

13ኛ ሳምንት ዛሬ ፍፃሜውን ሲያገኝ። ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን አስተናግዶ 1-1 ከተጠናቀቀ በኋላ ሁለቱም ቡድኖች ለብዙሀን መገናኛ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ስትራቴጂ መቀየር ካስፈለገ ኳስ ተጫዋች መለወጥ ያስፈልጋል” (ካሳዩ አራጌ ኢትዮጵያ ቡና)

ስለጨዋታው

“ጨዋታው በአጠቃላይ ጥሩ ነው። በአጠቃላይ የምለው ነገር ሂደቱን መታገስ ይገባል። በየሰከንዱ ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል መድረስ አይቻልም። መድረስ ይቻላል ግን አስተማማኝ አይደለም። ይሄ ነው ተጫዋቾች ላይ ጫና የፈጠረው። ተጫዋቾቹ በነፃነት እንዲጫወቱ ማድረግ አለብን። ከውጤት መራራቅ ስላለ በሁለተኛው አጋማሽ መጣደፍ ውስጥ ገብተዋል። የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ተጭነን ተጫውተናል። በሁለተኛው አጋማሽ የኛ ሜዳ ላይ ተጭነው ተጫውተዋል። በዚህ አይነት መንገድ ሲመጣ ለመውጣት ይቸግራል። በዛ ሰዓት በሚኖሩ ሂደቶች የሚበላሹ ኳሶች ይኖራሉ።”

ቡና ሁለተኛ ስትራቴጂ አያስፈልገውም ?

“ሁለተኛ ስትራቴጂ የሚባለው ነገር የተጫዋች ለውጥ ያስፈልጋል። ስትራቴጂ መቀየር ካስፈለገ ኳስ ተጫዋች መለወጥ ያስፈልጋል።”
ስለጨዋታው

ለጨዋታው ይዘነው የገባነው አጨዋወት ተጫዋቾቼ ለመተግበር የሚችሉትን ያህል ጥረት አድርገዋል (ደግአረግ ይግዛው ወልቂጤ ከተማ)

ስለጨዋታው

እንግዲህ ለፕሪምየር ሊጉ እንግዳ እንደመሆናችን መጠን። ጠንካራ ጨዋታ ነበር። ቡና ትልቅ ደጋፊ ያለው ክለብ ነው። ለጨዋታው ይዘነው የገባነው አጨዋወት ተጫዋቾቼ ለመተግበር የሚችሉትን ያህል ጥረት አድርገዋል። በርግጥ በመጀመሪያው አጋማሽ እንፈለግነው መንቀሳቀስ አልቻልንም። በሁለተኛው አጋማሽ ግን ችግሮቻችንን ፈተን በተቻለን መጠን ተጭነን ለመጫወት ያደረግነው ጥረት ቢኖርም።ባሰብነው ልክ ደግሞ ግብ ማግኘት አልቻልንም። በአጠቃላይ ግን ከጠንካራው ቡና ጋር ቢሆንም። ተጫዋቾቼ ባደረጉት እንቅስቃሴ ለወደፊቱ ተስፋ የሚሰጥ ነው። በቀጣይ ድክመቶቻችን እያየን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነን እንቀርባለን።

Muluken Tesfaye

Editor at Hatricksport website

Facebook

Muluken Tesfaye

Editor at Hatricksport website