ኢትዮኤሌክትሪክ አሰልጣኛ አሸናፊ በቀለ በነገው እለት በይፋ የአሰልጣኝነት ስራቸውን ይጀመራሉ፡፡
ኤትዮ ኤሌክትሪክን ከአምና ጀምሮ በዋና አሰልጣኝነት ሲመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ብርሀኑ ባዬ ዛሬ የመጨረሻ ልምምድ ቢያሰሩም ከነገው እለት ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት የቆዩት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመረከብ ከተጫዋቾቻቸው ጋር በመተዋወቅ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን በነገው እለት 09:00 ሰዓት እንደሚጀምሩ የሀትሪክ የውስጥ ምንጮች ተናግረዋል ፡፡
አሰልጣኝ አሸነፊ በቀለ አዳማ ከተማን፤ሲዳም ቡናን፤ንግድ ባንክን፤የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማሰልጠናቸው እሚታወስ ነው፡፡
ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሊጉ በ6 ጨዋታዎች በ 5 ነጥብ የሊጉ ደረጃ 15 ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
አስተያየት ይስጡ