መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ ወልድያ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር ድል ቀንቷቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ ወልድያ ከተማ እና ጅማ አባጅፋር ድል ቀንቷቸዋል፡፡

አጋራ
አጋራ

በ2010 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ ዛሬ ጅማሬውን ሲድረግ ወልድያ ከተማ እና ከከፍተኛ ሊግ ያደገው ጅማ አባጅፋር የመጀመሪያ 3 ነጥብ ማስመዝገብ ሲችሉ አርባምንጭ ከተማ እና መቐለ ከተማ አቻ ተለያተዋል፡፡ በሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታዲየም ጨዋታውን ያደረገው ወልድያ ከተማ በ73ኛው ደቂቃ በአንዱአለም ንጉሴ(አቤጋ) በፍጹም ቅጣት ምት እና 90ኛው ደቂቃ ላይ በኤዶም ኮድዞ 2 ግቦች ታግዞ አዳማ ከተማን በማሸነፍ የመጀመሪያ 3ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡ መከላከልን ምርጫው አድርጎ የተጫወተው አዳማ ከተማ በአጥቂዎች ኳስን በአግባቡ መጠቀም ባለመቻላቸው ምክንያት ለመሸነፍ ተገዷል፡፡

በ2ኛው ጨዋታ ጅማ አባጅፋር እና ሀዋሳ ከተማ የተገናኙ ሲሆን አዲስ አዳጊዎቹ ጅማ አባጅፋሮች ጃክ አፎላቢ በ 89 እና 91ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራቸው ግቦች 2-0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ በዚህ ጨዋታ 2ኛው ግብ መቆጠር በኋላ ረዳት ዳኛው በፕላስቲክ የውሀ እቃ መጠጫ በመመታታቸው ጨዋታው ለመቋረጥ ተገዶ ነበር፡፡ ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ ጨዋታው በድጋሚ ተጀምሮ በዛው ውጤት ተጠናቋል፡፡

በሌላ ጨዋታ አዲስ አዳጊው መቐለ ከተማ ወደ አርባምንጭ ተጉዞ 1 ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለምንም ግብ 0-0 የተጠናቀቀ ሲሆነ ይሄ ነው የሚባል የረባ እንቅስቃሴ ሳይስተዋልበት ተጠናቋል፡፡
ፕሪምየር ሊጉ ነገ ሲቀጥል በ9 ሰዓት ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ከፋሲል ከተማ ሲገናኙ ሰኞ ደደቢት ከ ወላይታ ዲቻ ማክሰኞ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ መከላከያ በተመሳሳይ 11፡30 ሲል በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ለብሔራዊ ቡድኑ 3 እና ከዛ በላይ ተጫዋቾችን ያስመረጡት ቅ/ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር የሚያደርጏቸው ጨዋታዎች ቀንና ሰዓት ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...