መነሻ ገጽ አፍሪካ በፊፋ የአለም ሀገራት ወርሀዊ ደረጃ ኢትዮጵያ በስምንት ደረጃዎች አሽቆለቆለች
አፍሪካዜናዎች

በፊፋ የአለም ሀገራት ወርሀዊ ደረጃ ኢትዮጵያ በስምንት ደረጃዎች አሽቆለቆለች

አጋራ
አጋራ

በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ኢትዮጵያ ስምንት ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 145ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
ኢትዮጵያ መጋቢት ወር ላይ ከነበረችበት 137ኛ ደረጃ 8 በማሽቆልቆል ነው 145ኛ ደረጃን የያዘችው፡፡
ከአፍሪካ ደግሞ 41ኛ ደረጃ ላይ መሆኗን ፊፋ በድህረገፁ አስፍሯል።
ቱኒዚያ ዘጠኝ ደረጃዎችን በማሻሻል በዓለም 14ኛ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከአፍሪካ አንደኛ ሆናለች።

ሴኔጋል አንድ ደረጃ በመቀነስ ከዓለም 28ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 2ኛ ደረጃን ስትይዝ፥ ዴሞክራቲክ ኮንጎ ከዓለም 38ኛ ከአፍሪካ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በአፍሪካ ደረጃ
ሞሮኮ፣ ግብፅ፣ ናይጀሪያ፣ ካሜሩን፣ ጋና፣ ቡርኪናፋሶና ኬፕ ቨርዴ በቅደም ተከተል ከ4ኛ እስከ 10ኛ ያለን ደረጃ ይዘዋል።

ባለፈው ወር ከነበሩበት በዚህ ወር ብዙ ያሽቆለቆሉ ሀገራትም ይፋ ሆነዋል፤ ሃይቲ 23፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ 21 እንዲሁም ኒካራጓ 20 ደረጃዎችን ዝቅ ብለዋል።

በፊፋ ወርሃዊ ሰንጠረዥ ቶንጋ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ባህማስ እና አንጉሊያ የመጨረሻውን 207ኛ ደረጃ ይዘዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ አስፈረመ

መሳይ አያኖ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ዘብ ሆኗል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...