መነሻ ገጽ AFCON Q በኬንያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ መረጋጋት የለም፡ ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ ሴባስቲያን ሚኜ ከኢትዮጵያው ጨዋታ በፊት ቡድኑን ሊለቁ ይችላሉ፡፡
AFCON Qአፍሪካዜናዎች

በኬንያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ መረጋጋት የለም፡ ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ ሴባስቲያን ሚኜ ከኢትዮጵያው ጨዋታ በፊት ቡድኑን ሊለቁ ይችላሉ፡፡

አጋራ
አጋራ

መንበራቸውን ከቀድሞው ቤልጀማዊው አሰልጣኝ ፖል ፒዩት የተረከቡት ከአራት ወራት በፊት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የሃገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከተቀጠሩ ጀምሮ የከፈላቸው የሁለት ወራት ደሞዝ ብቻ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የሐምሌና የነሃሴ ወር ደሞዝ እስካሁን አልተከፈላቸውም፡፡

ሴባስቲያን ሚኜ በባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ የሐራምቤ ከዋክብቱን የመሩ አምስተኛ የውጭ ሃገር አሰልጣኝ ናቸው፡፡ ሚስተር ሚኜ በፌዴሬሽኑ አሰራር መንገፍገፋቸውን የተረዳው የኬንያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ምትካቸውን ካሁኑ ማፈላለግ ጀምሯል፡፡ ከለቀቁም መንበራቸውን የአሁኑ የጎር ማህያ አሰልጣኝ ዳይላን ኬር ሊረከቡት ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ለጎር ማያ ክለብ የሰውዬውን የትምህርትና የሥራ ማስረጃ እንዲልኩለት ደብዳቤ መጻፉ፡፡ የኬንያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአሰልጣኙ ስምንት ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ ባለዕዳ ነው፡፡
የብሔራዊ ቡድኑ ዕዳ ይህ ብቻ አይደለም፤ የማላዊን የወዳጅነት እና የጋናን የማጣሪያ ጨዋታ ካሸነፋችሁ ተብሎ የተገባላቸው እጅ መንሻ እስካሁን ያልተከፈላቸው የሐራምቤ ከዋክብት ቃል የተገባልንን አስራ ዘጠኝ ሚሊዮን ሽልንግ ወዴት ዘወር አደረጋችሁብን ብለው ፌዴሬሽኑ ላይ መጉረጥረጣቸውን ቀጥለዋል፡፡

በፌዴሬሽኑ ሥነ-ምግባር እጅግ የተበሳጩት ፈረንሳያዊ ከበር ቆመዋል፤ ሁለት ሶስት ጊዜም መልቀቂያቸውን ለማስገባት ሞክረው እንደነበር ነው የተገለጸው፡፡ አሰልጣኙ ደሞዛቸው በቅርቡ ካልተሰጣቸውም ከዚህ በፊት የሃገሪቱን ብሔራዊ ቡድን እንዳሰለጠኑት ስኮትላንዳዊው ቦቢ ዊሊያምሰን እና ቤልጀማዊው አዴል አምሩሽ እሳቸውም ፌዴሬሽኑን ችሎት ፊት ገትረው ለመቀበል ያስባሉ፡፡
መስከረም 30 ባህር ዳር ላይ እንዲሁም ከሶስት ቀናት በኋላ ጥቅምት 3 ቀን ናይሮቢ ላይ ኢትዮጵያን የሚገጥመው ቡድን ለደርሶ መልሱ ጨዋታ ማትጊያ 26 ሚሊዮን ሽልንግ ቃል ቢገባለትም ተጫዋቾቹ ግን ጽድቁ ቀርቶ በቅጡ በተኮነንን እያሉ ነው፡፡ ለማንኛውም ጋናን 1-0 በረታው የኬንያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የሚሰማው ነገር ፌሽታ ብቻ አይመስልም፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...