መነሻ ገጽ ኦሮሚያ ዋንጫ በኦሮሚያ ዋንጫ የሁለተኛ ቀን ውሎ ሰበታ ምድብ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል 
ኦሮሚያ ዋንጫዜናዎች

በኦሮሚያ ዋንጫ የሁለተኛ ቀን ውሎ ሰበታ ምድብ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል 

አጋራ
አጋራ

ለ6ኛ ግዜ የሚካሄደው የኦሮሚያ ሲቲ ካኘ ዋንጫ የሰበታ ምድብ የሁለተኛ ቀን ውሎ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል ፡፡

በ8 ሰዓት  የተገናኙት በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ የሚመራው ሰበታ ከተማ እና በወጣቱ አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ የሚመራው ለገጣፎ ከተማ ሲሆኑ ጨዋታው ያለግብ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት መለያየት ችለዋል፡፡ 

በጨዋታው የመጀመሪያ  እና በሁለተኛው  አጋማሽ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ጥንቃቄ የበዛበት እና ብዙም የጎል ሙከራ ያልታየበት እንዲሁም የሜዳው የመሀል ክፍል ላይ የሚመላለሱና የሚጠለዙ ኳሶች ተስተውሎበታል  ፡፡
በጨዋታው 62ኛ ደቂቃ ላይ የሰበታ ከተማው ዜናው ፈረደ ከግብ ክልሉ ወጪ የመታውና የጎሉን አግዳሚ የመለሰበት ኳስ  የሚጠቀስ  የጎል አጋጣሚ ነበር፡፡  

ልክ 10:10 ሲል የተጀመረው የጅማ አባቡና እና ተጋባዡ ኢትዮጵያ መድንን ሲያገናኝ  ሳቢ እና ማራኪ ፣ጨዋታ ማድረግ ችለዋል፡፡
ጨዋታውን ያስጀመረችው ኢንተርናሽናል አርቢትር አስናቀች ገብሬ ስትሆን፡ ጨዋታው  እንደተጀመረ ደጋግመው ወደ ጎል መድረስ የቻሉት ኢትዮጵያ መድኖች ሲሆኑ  በአማካይ ስፍራ ተጨዋቾቻቸው አብርሀም ታምራት እና አዳማ ሳሙኤል ያደረጓቸው የግብ ሙከራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በ10ኛ ደቂቃ ላይ በጅማ አባቡና ተጫዋቾች በተሰራ ጥፋት በሚስማር ተራ በኩል 16.50 ላይ የተገኘችውን የቅጣት ምት አዳነ አየለ በድንቅ ሁኔታ ኳስዋን ከመረብ አገናኝቶ ኢትዮጵያ መድንን መሪ ማድረግ ችሏል፡፡

ከጎልዋ  መቆጠር በኃላ በአንጋፋው አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሐንስ የሚመሩት ጅማ አባቡናዎች ተጭነው  ሲጫወቱ በ31ኛ ደቂቃ ላይ በተገኘች  ቅጣት ምት ሐይደር ሸረፋ ሲመታ የኢትዮጵያ መድን በረኛ ተስፋዬ በቃና ኳስዋን ለመያዝ በሞከረበት ቅጽበት ኳስዋን መቆጣጠር ተስኖት  ኳስዋ ልትቆጠር ችላለች፡፡  

በዚሁ የመጀመሪያው አጋማሽ ሁለቱ ቡድኖች 1-1 በሆነ ውጤት ጨዋታውን አጠናቀዋል ፡፡ በሁለተኛው የጨዋታ  45 ላይ በደረጄ በላይ የሚመራው  ኢትዮጵያ መድን በፊት አጥቂያቸው አብደልአዚዝ ኡመር  ያልተሳኩ የጎል ሙከራዎች ማድረግ ችለዋል፡፡  በአንጻሩ ጅማ አባቡናዎች አፈግፍገው በመልሶ ማጥቃት ጨዋታን መጫወት ችለዋል፡፡
በኢትዮጵያ መድን በኩል ወጣቱ የአማካይ ተከላካይ ክፍል ተጫዋቾች አሚር ሙደሲር  የመሀል ክፍሉን የማረጋጋት ስራን በተገቢው ሲወጣ ተስተውሏል፡፡

የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ በመጀመሪያው 45 በተቆጠሩ ግቦች በአቻ ውጤት 1-1  ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

 
     ክለብ            ተጫወተ ጎ/ል          ነጥብ  1.ለገጣፎ ከተማ       2        1            4
 2.ሰበታ ከተማ          2         0            2
 3.ጅማ አባቡና          2         0            2
 4.ኢት.መድህን          2       -1            1

ጨዋታዎች ሐሙስ ሲቀጥሉ

ለገጣፎ ከ ጅማ አባቡና

ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን

በ8 እና በ10 ሰዓት የሚደረጉ ይሆናል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...