መነሻ ገጽ ኦሮሚያ ዋንጫ ​በኦሮሚያ ዋንጫ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባቡና ለፍፃሜ ደረሡ
ኦሮሚያ ዋንጫዜናዎች

​በኦሮሚያ ዋንጫ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባቡና ለፍፃሜ ደረሡ

አጋራ
አጋራ

የኦሮሚያ ሲቲ ካፕ የሶስተኛ ቀን ሁለት ጨዋታዎች የተከናወኑ ሲሆን ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባቡና ለፍፃሜ ተፋላሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በቅድሚያ 8 ሰዓት  የተገናኙት ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን ሲሆኑ በመጀመሪያው አጋማሽ  ሰበታ ከተማ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች አሸነፈው ወጠዋል፡፡ በአጫጭር ኳሶ መሀል ሜዳ ላይ ጥሩ የኳስ ቅብብል በተስተዋለበት በዚህ ጨዋታ ሰበታ ከተማ ተጭነው በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ችለዋል፡፡

 በ9ኛው እና በ39 ደቂቃ ላይ ጥሩ ሆኖ የዋለው አብይ ቡልቲ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ለዋንጫው ጨዋታ እንዲደርሱ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ፎቶ አብዬ ቡልቲ 
በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ከመጀመሪያው አጋማሽ በወረደ አቋም ሲጫወቱ ተስተውለዋል ፡፡ በዚሁ በመጀመሪያው 45 በተቆጠሩ ሁለት ግቦች ሰበታ ከተማ 2-0 በሆነ ውጤት ኢትዮጵያ መድህንን መርታት ችለዋል፡፡
10:10 ሲል በርካታ ደጋፊዎች በታደሙበት የጅማ አባቡና እና የለገጣፎ ከተማ ጨዋታ ጠንካራ የመሸናነፍ ፍክክር በታየበት ፍልሚያ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በ86 ኛ ደቂቃ ላይ የጅማ አባቡናው ጀሚል ያእቆብ ባስቆጠራት ጎል ቡድኑን ለእሁዱ የፍፃሜ ጨዋታ ማደርስ ችሏል፡፡

አራት ቡድኖች በሚሳተፉበት የኦሮሚያ ዋንጫ በነጥብ የተሻሉት 1እና2 የሆኑ ቡድኖች ለዋንጫ ሲፋለሙ፤3ኛ እና 4ኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖች ደግሞ ለደረጃ እሚጫወቱ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሠረት በደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት እና በነጥብ እና በጎል ክፍያ ለዋንጫ እና ለደረጃ እሚጫወቱ ይሆናል

ክለብ            ተጫወተ ጎ/ል          ነጥብ  

1.ሰበታ ከተማ      3         2             5

2. ጅማ አባቡና    3         1              5

 3.ለገጣፎ ከተማ  3         0            4

 4.ኢት.መድህን     3       -3            1

እሁድ ጥቅምት 19 ቀን 2009 

በ8:00 ሰዓት ለደረጃ

ለገጣፎ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን 

በ 10:00 ሰዓት ለዋንጫ

ሰበታ ከተማ ከ ጅማ አባቡና እሚፋለሙ ይሆናሉ

#በሰበታ እስታዲየም

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...