መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል። 
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል። 

አጋራ
አጋራ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ(እሁድ) ሲደረጉ ሀዋሳ ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ሲያሸንፉ ሌሎቹ ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።
አዳማ ላይ የተካሄደው አዳማ ከተማ እና ደደቢትን ያገናኘው ጨዋታ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል። ጥሩ እንቅስቃሴ በታየበት በዚህ ጨዋታ አዳማ ከተማ የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል። 8ኛው ደቂቃ ላይ የደደቢቱ ሽመክት ጉግሳ ሁለት የአዳማ ተጫዋቾችን አልፎ ይዞ የገባውን ኳስ ጃኮ ፔንዜ በቀላሉ ያዳነበት የሚጠቀስ ሙከራ ነበር። 15ኛው ደቂቃ በረከት ደስታ ከዳዋ ሁቴሳ ጋር 1-2 ተቀባብሎ የሞከረውን ኳስ ክሌመንት በግሩም ሁኔታ አድኖታል።

22ኛው ደቂቃ ላይ የአዳማ ከነማው ከነዓን ማርከነህ ከ17 ሜትር ላየሸ የሞከረው ኳስ የጎሉን ብረት ታኮ ሊወጣ ችሏል። 32ኛው ደቂቃ ላይ አቤል እንዳለ የአዳማውን ምኞት ደበበን አታሎ ለሽመክት ያሻገረለት ኳስ ወደ ወጪ ወቷል። 44ኛው ደቂቃ ላይ ሽመክት ጉግሳ ከ ግራ መስመር የተሻገረለትን ኳስ ሞክሮት በግቡ አናት ላይ ወጥቶበታል። 
70ኛው ደቂቃ ላይ ተስፋዬ ነጋሽ በሽመክት ጉግሳ ላይ በሰራው ጥፋት በሁለት ቢጫ ከሜዳ ሊሰናበት ችሏል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ሱራፌል ዳኛቸው ቦታውን ሸፍኖ ለመጫወት ተገዷል፡፡

76ኛው ላይ ሱሌይማን መሀመድ  ከርቀት የሞከረው ኳስ እንዲሁም 84ኛው ደቂቃ ላይ ሙጂብ ቃሲም ለጎል ቀርቦ የመታውን ኳስ ክለሜንት በግሩም ሁኔታ አውጥቶባቸዋል።

———————————-
በሌሎች ጨዋታዎች መቐለ ላይ በጉጉት የተጠበቀው የትግራይ ደርቢ መቐለ ከተማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲን አገናኝቶ ያለምንም ግብ 0-0 ተጠናቋል። 


 ይርጋለም ላይ አርባምንጭ ከተማን  ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ላኪ ሳኒ ባስቆጠረው ግብ 1-0 ሲመራ ቆይቶ 70ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ግደይ ባስቆጠረው ግብ በሜዳው ከሽንፈት ድኗል።

 ሀዋሳ ላይ ወልድያ ከተማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ በ ዳዊት ፍቃዱ 3 ግቦች እና ያቡን ዊሊያም ግብ 4-1 ማሸነፍ ችሏል። ኤዶም ሆውሶሮቪ ወልድያ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አስቆጥሯል። 
ድሬዳዋ ስታዲየም ላይ አዲስ አዳጊውን ጅማ አባጅፋርን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ አትረም ኩአሜ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ 1-0 በማሸነፍ ጣፋጭ 3ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...