በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ቀጥለው ተደረገዋል፡፡
በመብራት መቆራረጥ ምክንያት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አዲስአበባ ስታዲየም እሚደረጉ የ9 ሰዓት ጨዋታዎችን 30ደቂቃ ቀደም ብለው እንዲጀመሩ ማደረጉን ተከትሎ፡፡ 8:30 ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከፋሲል ከተማ ሲገናኙ ፋሲል ከተማዎች አጥቂው ኤዶም ሆውሶሮቪ ከዕረፍት መልስ ባስቆጠራት ጎል 1 ለ 0 አሸንፈው ውጥተዋል።
ወልድያ ላይ ወልድያ ከወላይታ ዲቻ ያደረጉት ጨዋታ በወልድያ 1 ለ 0 አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ሃብታሙ ሸዋለም ግቧን አስቆጥሯል።
አርባ ምንጭ ከተማ ላይ በ ጨዋታ ባለሜዳው አርባምንጭ ከተማ በድሬዳዋ ከተማ ሁለት ለባዶ ተሸነፏል፡፡
በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በ40ኛው ደቂቃ ላይ የድሬዳዋ ከነማው ዮሴፍ ዳሙዬ ባስቆጠራት ግብ 1-0 እየመራ ለእረፍት ወጥተዋል።
ከዕረፍት መልስም በ86ኛው ደቂቃ የድሬዳዋ ከነማ 18 ቁጥሩ በረከት ይስሃቅ ሁለተኛውን ጎል በማስቆጠር ቡድኑ የጨዋታ የበላይነቱን እንደያዘ ውድድሩን እንዲያጠናቅቅ አደርጓል።
በጨዋታው ድሬዳዋ ከተማዎች ፍጹም የጨዋታ የበላይነትን ያሳዩበት ሲሆን በአንጻሩ አርባምንጭ ከተማ ደግሞ በሜዳው በተከታታይ ሁለት ጊዜ በመሸነፍ ስጋት ውስጥ ገብቷል ፡፡
ሃዋሳ ላይ ሃዋሳ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በሃዋሳ 3 ለ 2 አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል።
ጃኮ አረፋት፣ ፍሬው ሰለሞን እና ታፈሰ ሰለሞን ለሃዋሳ ጎሎችን ሲያሰቆጥሩ አዲስ ግደይ ደግሞ ለሲዳማ ቡና ሁለቱን ጎሎች ከመረብ አገናኝቷል።
ጅማ ላይ የተደረገው ጅማ አባ ቡና ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ሲጠናቀቅ፥ በድሉ መርዕድ ለጅማ አባ ቡና ዳዋ ሁቴሳ ደግሞ ለአዳማ ከተማ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
10:30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የተደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ደደቢት ጨዋታ ብቸኛው ጎል ያልተቆጠረበት ጨዋታ በመሆን አቻ ተጠናቋል።
የደረጃ ሰንጠረዥ ይመልከቱ
| # | ክለብ | ተጫ | ልዩ | ነጥብ |
|---|---|---|---|---|
| 1 | ደደቢት |
23 | 14 | 40 |
| 2 | ቅዱስ ጊዮርጊስ |
21 | 19 | 39 |
| 3 | ሲዳማ ቡና |
23 | 6 | 39 |
| 4 | አዳማ ከተማ |
23 | 4 | 36 |
| 5 | ኢትዮጵያ ቡና |
22 | 9 | 35 |
| 6 | ፋሲል ከተማ |
22 | 2 | 35 |
| 7 | ሀዋሳ ከተማ |
23 | 3 | 31 |
| 8 | |
23 | 0 | 28 |
| 9 | አርባምንጭ ከተማ |
22 | -1 | 29 |
| 10 | ድሬዳዋ ከተማ |
23 | -4 | 28 |
| 11 | ኢትዮ ኤሌክትሪክ |
23 | 1 | 27 |
| 12 | ጅማ አባቡና |
21 | -4 | 24 |
| 13 | መከላከያ |
22 | -13 | 24 |
| 14 | ወላይታ ድቻ |
23 | -11 | 23 |
| 15 | ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ |
23 | -13 | 20 |
| 16 | አዲስ አበባ ከተማ |
22 | -12 | 16 |
















አስተያየት ይስጡ