በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ጨዋታ በሊጉ ጅማ አባጅፋር ድል ሲቀናው ወልዲያ ከተማ ከ ሀዋሳ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል።
በጅማ ስቴዲየም ዛሬ በተካሄደው 17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜሪሊግ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ድሬደዋ ከተማን አንድ ለ ባዶ አሸነፈ።
ለጅማ አባጅፋር ኦኪኪ አፎላቢ በ35ኛ ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ ነው ክለቡን አሸናፊ እንዲሆን ያስቻለው፡፡
በእለቱ ያስቆጠራት ግብ የጎል ቁጥሩን ወደ 10 በማሳደግ ኮከብ ግብ አግቢነቱን እንዲያጠናክር አስችሎታል፡፡
በጨዋታው ሁለቱ ቡድኖች ተመጣጣኝ የሆነ እንቅሰቃሴ አሳይተዋል፡፡
ጅማ አባጅፋር ማሸነፉን ተከትሎ በ28 ነጥብ 3 ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡
ሌላኛው ወልዲያ ላይ የተካሄድው የ17ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ከ ወልዲያ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ ወልዲያ ከተማዎች በባከነ ደቂቃ በምንያህል ተሾመ ወሳኝ ግብ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
በጨዋታው ጎል በማግባት ቀዳሚ የነበሩት እንግዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች ሲሆኑ በ51ኛ ደቂቃ ላይ በእስራኤል እሸቱ አማካኝነት ቀዳሚነቱን ቢወስዱም የኃላ ኃላ የጨዋታው 90 ደቂቃ ተጠናቆ በባከነ ሰዓት በምንያህል ተሾመ ግብ 1ነጥብ ተጋርተው ሊወጡ ችለዋል።
አስተያየት ይስጡ