መነሻ ገጽ ቅድመ ዳሰሳ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር
ቅድመ ዳሰሳዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር እንዲህ እንዲያ እያለ እነሆ 6ኛ ሳምንት ላይ ደርሷል። ሊጉ እስካሁን ድረስም ለ5 ሳምንታት በፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት እና እንግዳ ክለብን በመልካም አቀባበል እየተካሄደ ሲሆን ይህም ይበል የሚያስብል ሆኖ እስከ ሊጉ ፍፃሜ መቀጠል አለበት ብለን እናምናለን።

በሊጉ 6ኛ ሳምንት 8ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚካሄዱ ሲሆን አርብ እና እሁድ አንድ አንድ እንዲሁም ቅዳሜ ስድስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል። ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል 5ቱ ጨዋታዎች ክልል ላይ ሲደረጉ ቀሪዎቹ 3ጨዋታዎች ደግሞ አዲስ አበባ ላይ የሚደረጉ ይሆናል። ከነዚህ ጨዋታዎች መካከል ነገ(ቅዳሜ) አዳማ ላይ አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ቅድመ ዳሰሳ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን አቅርበንላችኋል። መልካም ንባብ።

ጨዋታ: አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር
የጨዋታ ቀን: ቅዳሜ ታህሳስ 24/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌዴራል አርቢትር ኢሳያስ ታደሰ
የጨዋታ ቦታ: አዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት ነገ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አዳማ ከተማ ከጅማ አባጅፋር የሚያደርጉት ጨዋታ 9:00 ላይ የሚጀምር ይሆናል። በ4ኛው ሳምንት የተለያየ ውጤት ያስመዘገቡት እነዚህ ሁለት ቡድኖች የነገውን ጨዋታ በጉጉት እንዲጠብቁት ተገደዋል። አዳማ ከተማ በ4ኛው ሳምንት መደ መቐለ አቅንቶ በስሑል ሽረ እስከ 86ኛው ደቂቃ ድረስ ሲመራ ቢቆይም 86ኛው ደቂቃ ላይ ዱላ ሙላቱ ባስቆጠራት ግብ 1-1 ተለያይቶ የተመለሰ ሲሆን ጅማ አባጅፋር በአንፃሩ በሜዳው በብዙአየሁ እንደሻው እና አምረላ ደልታታ ግብ ቅ/ጊዮርጊስን 2-1 ማሸነፉ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ አዳማ ከተማ ወደ ድል ለመመለስ ጅማ አባጅፋር ደግሞ የአሸናፊነት ጉዞውን ለማስቀጠል የሚያደርጉት ጨዋታ በመሆኑ በተመልካቹ ዘንድ በጉጉት እንዲጠበቅ አስችሎታል።

ሁለቱ ቡድኖች በ5ሳምንት የሊጉ ጉዞ በደረጃ ሰንጠረዡ በአንድ ነጥብ ብቻ ተበላልጠው የተቀመጡ ሲሆን ባለሜዳው አዳማ ከተማ በ7ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ተጋጣሚው ጅማ አባጅፋር ደግሞ በ1ነጥብ ብቻ አንሶ በ6ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ስለሆነም በጨዋታው በሚከሰተው ውጤት የደረጃ ለውጥ ሊመዘገብበት ይችላል። አዳማ የሚያሸንፍ ከሆነ ከተጋጣሚው በ4ነጥቦች በመራቅ ወደ መሪዎቹ መጠጋት ሲችል በአንፃሩ ጅማ ቢያሸንፍ ደግሞ ነጥቡን ወደ 9 በማሳደግ ከአዳማ በላይ እንዲቀመጥ ያስችለዋል። ይህንንም ተከትሎ የነገው ጨዋታ ከባድ ፉክክር ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...