መነሻ ገጽ መቐለ 70 እንደርታ ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ አ.ዩ.
መቐለ 70 እንደርታቅድመ ዳሰሳወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ አ.ዩ.

አጋራ
አጋራ

 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 5ኛ ሳምንት 7ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የተካሄዱ ሲሆን የመጨረሻው አንድ ጨዋታ ነገ(ሰኞ) የሚደረግ ይሆናል። ይህ የመጨረሻ ጨዋታ መቐለ ላይ መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ አ.ዩ. የሚያደርጉት ሲሆን ይህንንም ጨዋታ በዚህ ቅድመ ዳሰሳ ለእናንተ እንዲስማማ አድርገን አቅርበንላችኋል።

ጨዋታ
መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ አ.ዩ.
የጨዋታ ቀን: ሰኞ ታህሳስ 20/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ኢንተርናሽናል አርቢትር በላይ ታደሰ
ቦታ: መቐለ ኢንተርናሽናል ስታዲየም

በሊጉ የ5ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በመቐለ ኢንተርናሽናል ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታ ከወልዋሎ አ.ዩ. የሚያደርጉት ጨዋታ 9:00 ላይ የሚጀምር ይሆናል። ወልዋሎ አ.ዩ. የሊጉን መሪነት ለማስጠበቅ መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ ወደ ሊጉ አናት ለመጠጋት የሚያደርጉት ጨዋታ በመሆኑ በጉጉት ይጠበቃል።

በ4ኛው ሳምንት ሁለቱ ቡድኖች የተለያየ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን መቐለ 70 እንደርታ ወደ ሲዳማ አቅንቶ በአማኑኤል ገ/ሚካኤል እና በያሬድ ከበደ ሁለት ግቦች ታግዞ ሲዳማ ቡናን 2-1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ሲችል መቐለ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ላይ ጅማ አባጅፋርን ያስተናገደው ወልዋሎ አ.ዩ. ያለግብ አቻ ተለያይቶ በሊጉ የነበረዉን የ100% የማሸነፍ ጉዞ ማምከን ችሏል። ሁለቱ ቡድኖች በ4ሳምንት የሊጉ ጉዞ በደረጃ ሰንጠረዡ በሶስት ነጥቦች ተበላልጠው በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው ወልዋሎ አ.ዩ. በ10 ነጥቦች 1ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ የሚመራው መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ በ7ነጥቦች 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በነገው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ የሚያሸንፍ ከሆነ ከተጋጣሚው ጋር በነጥብ መስተካከል ሲችል በአንፃሩ ወልዋሎ ድል የሚቀናው ከሆነ ከተከታዩ ሲዳማ ቡና በ4ነጥቦች ርቆ መቀመጥ ይችላል።

በመቐለ በኩል ጉዳት ላይ የነበሩት ዮናስ ገረመው እና ዳንኤል ደምሱ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ አማካዩ ሚኬኤሌ ደስታ ግን አሁንም በጉዳት የነገው ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል። ወልዋሎዎች በነገው ጨዋታ አቼምፖንግ አሞስን በጉዳት ሲያጡ ካርሎስ ዳምጠው እና ፍቃዱ ደነቀ ከጉዳት ያገገሙ ተጫዋቾች ናቸው።

ሊጉን አንድ ጨዋታ የሚቀረው ወልዋሎ አ.ዩ. በ10 ነጥቦች ሲመራ ሲዳማ ቡና በ9 እንዲሁም ፋሲል ከተማ እና ባህርዳር ከተማ በእኩል 8ነጥቦች በግብ ክፍያ ተበላልጠው ተከታዮቹን ደረጃ ይዘዋል። ስሑል ሽረ፣ ድሬደዋ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና በ5፣ በ4 እና በ2 ነጥቦች በቅደም ተከተል ከ14ኛ እስከ 16ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። የኮከብ ጎል አግቢነቱን ደግሞ የፋሲል ከተማው ሙጂብ ቃሲም 4 ግቦች ሲመራ የኢትዮጵያ ቡናው እንዳለ ደባልቄ፣ የባህርዳር ከተማዎቹ ማማዱ ሲዲቤ እና ፍፁም ዓለሙ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማው ብሩክ በየነ በእኩል 4 ግቦች ሲከተሉ አዲስ ግደይ፣ ዳዋ ሁቴሳ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል፣ ይገዙ ቦጋለ እና ሰመረ ሀፍተይ በእኩል 3ግቦች ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...