መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ቅድመ ዕይታ | ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና
ሲዳማ ቡናቅድመ ዳሰሳዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

የጨዋታ ቅድመ ዕይታ | ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና

አጋራ
አጋራ

ቅድመ ዳሰሳ ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ቅዳሜ ሶስት ጨዋታ ሲደረግ ነገ ማለትም እሁድ ቀሪ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ከነዚህ ውስጥም በነገው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና የሚያደርጉትን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል፡፡

ጨዋታ: ፋሲል ከነማ ከሲዳማ ቡና
የጨዋታ ቀን: እሁድ ጥር 17/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢተር ተካልኝ ለማ
የጨዋታ ቦታ: አጼ ፋሲለደስ ስታድየም

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ላይ የደረሰ ሲሆን ባለፈው በዘጠነኛው ሳምንት ወደ ስሑል ሽረ ተጉዘው ባለቀ ሰዓት በተቆጠረባቸው ተከታታይ ጎሎች ነጥብ ጥለው የተመለሱትና ባለፉት ባደረጉዋቸው በሜዳቸው ጨዋታዎች ምንም ነጥብ ያልጣሉት የአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ፋሲል ከነማዎች በሜዳቸው ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳሉ፡፡

ባለ ሜዳዎቹ ፋሲል ከነማዎች እንደተለመደው የተወሰኑ የኳስ ንክኪዎችን በማድረግና ብዙ የጎል እድሎችን በመፍጠር ለተጋጣሚ ቡድን አደጋ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። ባንፃሩ እንግዳዎቹ ሲዳማ ቡናዎች እንደ ተለመደው ማራኪ የኳስ ፍሰት ያሳያሉ ተብሎ ይጠበቃል።በዚህም የተነሳ የነገው ጨዋታ በጉጉት እንዲጠበቅ ያደርገዋል።

ፋሲል ከነማዎች በአስራ አምስት ነጥብና በዘጠኝ ንፁህ ጎል ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፡፡ባንፃሩ ሲዳማ ቡናዎች በአስራ ሁለት ነጥብና በሁለት ንፁህ ጎል ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ባለ ሜዳዎቹ ፋሲል ከነማዎች ከእንግዶቹ ሲዳማ ቡናዎች በሶስት ነጥብና በሰባት ደረጃ ከፍ ብለው ተቀምጠዋል፡፡

የጉዳት ዜና ስንመለከት ባለሜዳዎቹ በፋሲል ከነማ በኩል አማካኞቻቸውን ሀብታሙ ተከስተንና ጅብሪል አህመድን በነገው ጨዋታ የማያሰልፉ ሲሆን የያሬድ ባየህ የመግባት ነገርም ያጠራጥራል፡፡ በሲዳማ ቡና በኩል ደግሞ ወንድሜነህ አይናለምና ሙልቀን ታሪኩ በጨዋታው የማያሰልፉ ሲሆን ጥሩ ዜና የሚልዮን ሰለሞን ከጉዳት አገግሞ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይገመታል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አዲዳስና ፑማ ያለበትን ቱታ በመልበሱ የተባረረው አርቢትር ..

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የጨዋታ ቀን አንድ አርቢትር ልምምድ ሲያደርግ የለበሰው...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...