የኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የዕለተ ሰኞ የአ/አ ስታዲየም ጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ
በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት የመጨረሻ 1ጨዋታ ዛሬ (ሰኞ) በአ/አ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።
10፡00 ሲል ወልዋሎ.አ.ዩ ከ ወልድያ ስፖርት ክለብ የሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠበቅ ነው። አዲግራት ላይ መካሄድ የነበረበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በአንዳንድ
ወልዋሎ.አ.ዩ ካለፉት 4 ጨዋታዎች ሁለቱን ጨዋታዎች ተሸንፎ ሁለቱን ደግሞ አቻ ተለያይቶ ከ4 ጨዋታዎች ማሸነፍ ተስኖት የውጤት ቀውስ ውስጥ ይገኛል። ወልድያ ስፖርት ክለብ በበኩሉ ካለፉት 4ጨዋታዎች ሶስቱን ተጫውቶ 1በማሸነፍ 1አቻ ወጥቶ 1ተሸንፏል። በ7ኛው ሳምንት ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ጋር በሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ በፀጥታ ችግር ምክንያት ወደ ጥር 24 2010ዓ.ም መዛወሩ የሚታወስ ነው።

ወልድያ ስፖርት ክለብ ካደረጋቸው 7ጨዋታዎች 4ቱን ከሜዳው ውጪ ያደረገ ሲሆን ዛሬ ወደ አ/አ ተጉዞ የሚያደርገው ጨዋታ 5ኛ ከሜዳው ውጪ የሚያደርገው ጨዋታ ይሆናል፡፡ ወልድያ ስፖርት ክለብ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ማሸነፍ አልቻለም። ሀዋሳ ላይ በሀዋሳ ከተማ 4-1 እንዲሁም አ/አ ስታዲየም ላይ በኢትዮጵያ ቡና 2-0 ተሸንፎ ጎንደር ላይ ከፋሲል ከተማ ጋር 0-0 እና ይርጋለም ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
ወልዋሎ.አ.ዩ በአንፃሩ በሜዳው 5 ጨዋታዎችን የተጫወተ ሲሆን ካደረጋቸው 5 የሜዳው ላይ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡናን 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት ያሸነፈበት ጨዋታ ብቸኛው በሜዳው ያስመዘገበው ድል ነው። በመከላከያ 1-0 ተሸንፎ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር እና ከሲዳማ ቡና ጋር በተመሳሳይ 0-0 እንዲሁም ከፋሲል ከተማ ጋር 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በአጠቃላይ በፕሪሚየር ሊጉ ወልዋሎ.አ.ዩ ካደረጋቸው 9ጨዋታዎች 2ጨዋታዎችን አሸንፎ በ5 አቻ ተለያይቶ 2ቱን ተሸንፎ 11 ነጥቦችን ሰብስቦ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልድያ ስፖርት ክለብ በአንፃሩ ማድረግ ከሚገባው 9ጨዋታዎች 7ቱን ብቻ አከናውኖ 2ጨዋታዎችን አሸንፎ 3ጨዋታዎችን አቻ ወጥቶ 2ጨዋታዎችን ተሸንፎ ማግኘት ከሚገባው 21ነጥቦች 9ኙን ብቻ አሳክቶ ከወራጅ ቀጠናው በነጥብ ብቻ ርቆ 12ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
ከወልዋሎ.አ.ዩ ካደረጋቸው በኩል በጉዳት በረከት አማረና ሙለአለም ጥላሁን በጡንቻ ጉዳት እንየው ካሳሁን በቅጣት እማይኖሩ ሲሆን በወልድያ በኩል ሲሆን ብሩክ ቃልቦሬ እና አማረ በቀለ በቅጣት ለቡድናቸው ግልጋሎት የማይሰጡ ይሆናል፡፡
አስተያየት ይስጡ