ስሑል ሽሬ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሀምን ሾሟል

ከቀናት በፊት ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር የተለያዩት ስሑላውያኑ አሰልጣኝ የሲሳይ አብርሀምን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ ሾመዋል።

 

ሼር ኢትዮጵያ፣አክሱም ከተማ፣ሰበታ ከተማ፣አዳማ ከተማ እና ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በረዳትነት ማሰልጠን የቻሉት ሲሳይ አብርሀም አምና አዳማ ከተማን ይዘው በአንደኛው ዙር 22 ነጥብ በመሰብሰብ 6ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ የቻሉ ሲሆን ከክለቡ ጋር ሳይስማሙ ቀርተው መለየያየታቸው ይታወሳል። 2004 ላይ አዳማን ይዘው ባስመዘገቡት ጥሩ ውጤት የተሻለ ኮንትራት ቀርቦላቸው አዳማን ለቀው ሲሼር ኢትዮጵያን ቢይዙም በወቅቱ ከሳቸው መልቀቅ በኋላ አዳማ የመውረድ ስጋት ስለተጋረጠበት ሁለት ጨዋታ ሲቀረው በድጋሚ ወደ አዳማ ከተማ በመመለስ ቡድኑን ከመውረድ ታድገውታል። በጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኙት ስሑል ሽሬዎች ጠንካራ ተፎካካሪ የማድረግ ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer