ስሑል ሽረ ዲድዬ ሌብሪን ከጅማ አባጅፋር አስፈረሙ
በሳምሶን አየለ ሚመሩት ስሑል ሽረ የክረምቱ ስድስተኛ ፈራሚያቸውን ከጅማአባጅፋር አድርገዋል።ባሳለፍነው ውድድር ዓመት ከጅማ አባጅፋር ጋር ያሳለፈው አይቮሪኮስታዊው የመስመር አጥቂ ከሁለት የመስመር አጥቂዎቻቸው ቢስማርክ ኣፒያ ና ቢስማርክ አፖንግ ለተለያዩት ስሑል ሽረዎች ጥሩ አማራጭ ሊሆናቸው አንደሚችል ይገመታል።
በተጨማሪ ስሑል ሽረዎች ባሳለፍነው ውድድር ዓመት ከሃብቶም ቢሰጠኝ እና ዳዊት አሰፋ ጋር እየተፈራረቀ የተጫወተውን ግብ ጠባቂው ሰንደይ ሮቲሚ ጋር ተለያይቷል።
አስተያየት ይስጡ