መነሻ ገጽ መከላከያ ሲዳማ ቡና መከላከያን በማሸነፍ ከወራጅነት ስጋት ሙሉ ለ ሙሉ ወጥቷል።
መከላከያሪፖርትሲዳማ ቡናየኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበርየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሲዳማ ቡና መከላከያን በማሸነፍ ከወራጅነት ስጋት ሙሉ ለ ሙሉ ወጥቷል።

አጋራ
አጋራ

ይርጋለም ላይ የተካሄደው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ከወራጅ ስጋት ሙሉ ለሙሉ ለመውጣት የተፋለሙበት ነበር። ሲዳማዎች በ28ኛው ሳምንት ይርጋለም ላይ መቐለን ካሸነፈው ቡድን 3 ቅያሪዎችን አድርገው ገብተዋል እነሱም ፍቅሩ ወዴሳ፣ ፍፁም ተፈሪ እና ይገዙ ቦጋለን በመሳይ አያኖ ትርታዬ ደመቀና አዲስዓለም ደበበ ናቸው። መከላከያም ወልድያን ካሸነፈው ቡድን ምንይሉ ወንድሙን በ በኃይሉ ግርማ እንዲሁም ሽመልስ ተገኝን በምንተስኖት አዳነ ቀይረዋል። የመጀመርያ 15 ደቂቃ ለተመልካች የሚስብ ጨዋታ ያልታየበት ነበር። ሆኖም ሲዳማዎች በአጥቂያቸው አዲስ ግደይ ላይ ትኩረት አድርገው ሲንቀሳቀሱ ነበር የዚህ ውጤትም 13ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ግዳይ ያለቀለት ኳስ ሞክሮ የመከላከያው ግብ ጠባቂ አቤል አምክኖበታል። እንዲሁም 18ኛው ደቂቃ ላይ ወንድሜነህ አይናለም አክርሮ የመታውን ኳስ አቤል ኳሱን ለማዳን በሚሞክርበት ግዜ በራሱ ግብ ላይ ልያስቆጥር ለጥቂት ብረቱን መቶ ወደ ውጭ ወጥቷል። የመጀመርያው አጋማሽ የሲዳማ በላይነት የታየበት ነበር። መከላከያዎች ይሄ ነው የሚባል ጠንካራ ሙከር ባያደርጉም አልፎ አልፎ የሲዳማ የግብ ክልል ላይ ሲደርሱ ነበር እነሱም ፍፁም ገ/ማርያምና ሳሙኤል ሳሊሶ ያደረጉዋቸው ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራ ብቻ ነበሩ።

2ኛው 45 ገና ጨዋታው በተጀመረ 46ኛው ደቂቃ ላይ አዲስ ግደይ የራሱን የግል ብቃት ተጠቅሞ አምስት ተጨዋቾችን በማለፍ ደጋፊዎችን ያስደመመች ግብ አስቆጥሯል። ጎሉን ተከትሎ አዲስ ግደይ በፕሪሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸውን የጎል ብዛት 12 ማድረስ ችሏል። ከ50ኛ ደቂቃ እስከ 75ኛ ደቂቃ ሲዳማ ቡና መከላከልን መሠረት አድርጎ ተጫውቷል። 67ኛው ደቂቃ ላይ ፍፁም ገ/ማርያም በመከላከያ በኩል ግብ የማግባት ወርቃማ እድል ኣግኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ሲዳማዎች ጎሉን ለማስጠበቅ በማሰብ መጃይድ መሃመድን በወንድሜነህ አናይለም በመቀየር ለመከላከል ተገዶ ነበር። መላከያዎችም አቻ ለመሆን የተሻለ ተንቀሳቅሰው ነበር። ሆኖም የአቻነት ግብ ሳያስቆጥሩ ጨዋታው በሲዳማ 1ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የአሰልጣኞች አስተያየት
የሲዳማው አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ “ተጨዋቾቼ ጥሩ ስነ ልቦና ላይ ስለ ነበሩና ጥሩ ስለተንቀሳቀሱ ውጤቱ ይገባናል፤ የደጋፊዎች ማህበሩንም ማመስገን ወዳለሁ፤ ከወራጅ ስትጋም ነፃ ነን።”

በ 29ኛው ሳምንት ሃሙስ 9 ሰዓት ይካሄዳል ተብሎ የነበረውና ባልታወቀ ምክንያት ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ሰበታ ላይ የተካሄደው የደደቢትና የወልድያ ጨዋታ ያለ ግብ አቻ ተጠናቋል። በውጤቱም መሰረት ወልድያዎች ወደ ከፍተኛው ሊግ መውረዳቸውን ሲያረጋግጡ ደደቢቶችም ሁለተኛው ዙር ላይ እያሳዩ ሚገኙትን ደካማ ኣቋም አስቀጥለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...