ሰበር ዜና:- ሊግ ካምፓኒው ዛሬ ባደረገው ስብሰባ አዳዲስ ውሳኔዎችን አስተላለፈ…..

 

#የዘንድሮ ውድድር ሙሉ ለሙሉ እንዳልነበረ ታሳቢ ተደርጓል

#ጥሎ ማለፍ የለም…..እና ሌሎችም

#በአህጉራዊ ውድድሮች ኢትዮጵያን የሚወክሉ ቡድኖች በደንቡ መሠረት ይስተናገዳል

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ካምፓኒ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
ከእነዚህ መካከል አንደኛው የ2012 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በCOVID-19 ምክንያት መቋረጡን ተከትሎ ውድድሩ መሠረዙ የሚታወስ ነው። ይህ በመሆኑ ውድድሩ ሙለ ለሙሉ እንዳልተካሄደ ታሳቢ ተደርጎ ከዚህ በኋላ ሊግ ካምፓኒው የሚወስናቸው ውሳኔዎች የተሰረዘውን ውድድር ከግምት ሳያስገባ ውሳኔ ማስተላለፍ ይገኝበታል።

#75 በመቶና ከዚያ በላይ

ከዚህ በተጨማሪ ውድድሩ መሠረዙን ተከትሎ ሲያወዛግቡ ለነበሩ ጉዳዮች እልባት ለመስጠት ካለፈው ተሞክሮ በመነሳት በውድድር ደንብ ላይ መሻሻሎች ተደረገዋል። በዚህም መሠረት ሊጉ መቀጠል የማይችልበት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር በሚያጋጥምበት ግዜና ተሳታፊዎቹ 75 በመቶና ከዚያ በላይ የተጫወቱ እንደሆነ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ ቡድኖች በቀጣይ አመት ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግና በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይወክላሉ።
75 በመቶና ከዚያ በላይ ተጫውተው ወራጅ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲወርዱ ሲደረግ ሶስት ቡድኖች ደግሞ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያድጋሉ።

#ጥሎ ማለፍ የለም

ቀደም ባሉት አመታት በነበረው አሠራር በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የሚወክለው ቡድን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ የሚያነሳው ቡድን እንደነበር ይታወቃል። ነገር ግን ሊግ ካምፓኒው ዛሬ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የጥሎ ማለፍ ውድድር የማይኖር ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ሆኖ የሚያጠናቅቀው ቡድን በኮንፌደሬሽን ዋንጫ የሚሳተፍ ይሆናል።

#በ2021 ዓ.ም ኢትዮጵያን ማን ይወክላታል?

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በ2021የክለብ ውድድሮችን የሚያደርግ ከሆነና ተሳታፊዎቹን አሳውቁኝ የሚል ከሆነ ዛሬ በፀደቀው ደንብ መሠረት ለማሳወቅ ወስኖ ወጥቷል።

16/11/2012 ዓ.ም