መነሻ ገጽ ዜናዎች ሪፖርት | የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ እድላቸውን አስፍተዋል።
ዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

ሪፖርት | የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ወደቀጣዩ ዙር ለማለፍ እድላቸውን አስፍተዋል።

አጋራ
አጋራ

እ.አ.አ በ2020 ቶኪዮ ላይ ለሚደረገው ኦሎምፒክ እና ከ23 አመት በታች ለሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያውን ከሶማሊያ አቻው ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ቡድን 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

10:03 ሲል የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በኢትዮጵያ የበላይነት ሊጠናቀቅ ችሏል። በጨዋታውም ቀይ ቀበሮዎቹ የመጀመሪያውን ሙከራ ለማድረግ 3ደቂቃዎች ብቻ ነበር የፈጀባቸው። 3ኛው ደቂቃ ላይ ከንዓን ማርክነህ ወደ ሳጥን ይዞት የገባውን ኳስ ሞክሮት የግቡን አግዳሚ ታካ ወጥታለች። ከዚህች ሙከራ 13ደቂቃዎች በኋላ 16ኛው ደቂቃ ላይ የሐዋሳ ከተማው እስራኤል እሸቱ ሳጥን ውስጥ ያገኘውን ኳስ አክርሮ መቶት ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል። በጨዋታው ላይ አልፎ አልፎ ወደ ኢትዮጵያ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት ያደርጉ የነበሩት የሶማሊያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን አጨዋወታቸው የተደራጀ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድንን ጫና ውስጥ መክተት ሳይችሉ ቀርተዋል።

21ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያው ዳዊት ማሞ የተገኘውን ቅጣት ምት በቀጥታ ሞክሮት የሶማሊያው ግብ ጠባቂ ዓሊ በድንቅ ሁኔታ አድኖበታል። ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በተደጋጋሚ መድረስ የቻሉት ቀይ ቀበሮዎቹ የመጀመሪያውን ግብ ለማስቆጠር 28 ደቂቃዎች መጠበቅ ነበረባቸው። 28ኛው ደቂቃ ላይ በረከት ላይ የተሰራውን ጥፋት ጥፋት ተከትሎ የተገኘውን የቅጣት ምት ዳዊት ማሞ ወደ ግብ አሻምቶት ከነዓን ማርክነህ በቀላሉ አስቆጥሯል። ከግቡ መቆጠር በኋላ የሶማሊያ ብሔራዊ ቡድን በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ጥረት ቢያደርጉም ውጤታማ መሆን አልቻሉም። የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 6 ደቂቃዎች ሲቀሩት 39ኛው ደቂቃ ላይ የመከላከያው ቴዎድሮስ ታፈሰ ያሻገረለትን ኳስ እስራኤል እሸቱ ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል። ከዚህ ግብ መቆጠር በኋላ ይሄ ነው የሚባል የረባ እንቅስቃሴ ሳይደረግበት የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል።

ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ የሶማሊያ ከ23 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጫና ፈጥረው የተጫወቱ ሲሆን የመጀመሪያውን ሙከራ ለማድረግ 4ደቂቃዎች ብቻ ነበር የፈጀባቸው። 49ኛው ደቂቃ ላይ የሶማሊያው ፋይሰል ሀሺ እንዲሁም 58ኛው ደቂቃ ላይ አበዲአዚዝ አቶሽ የሞከሯቸውን ኳሶች የኢትዮጵያው ግብ ጠባቂ ተክለማርያም ሻንቆ አድኗቸዋል። 66ኛው ደቂቃ ላይ የሶማሊያው ተከላካይ አብዱዌሊ መሀመድ ተቀይሮ የገባው አማኑኤል ገ/ሚካኤል ላይ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የፍጹም ቅጣት ምት ራሱ አማኑኤል ገ/ሚካኤል አስቆጥሮ የኢትዮጵያን መሪነት ወደ 3-0 ከፍ ማድረግ ችለዋል። ከ4ደቂቃዎች በኋላ 70ኛው ደቂቃ ዳዊት ማሞን ቀይሮ የገባው አቡበከር ሳኒ ከከነዓን ማርክነህ የተሻገረለትን ኳስ አስቆጥሮ ኢትዮጵያን አሸናፊ ማድረግ ችሏል። ሆኖም አቡበከር ግቧን ካስቆጠረ ከ 5ደቂቃዎች በኋላ የሶማሊያው መሀመድ አሊ ላይ በሰራው ከባድ ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል። ጨዋታዉም በኢትዮጵያ 4-0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ሰኞ ህዳር 10 2011ዓ.ም ጅቡቲ ላይ የሚደረግ ይሆናል።

የአሰልጣኞች አሰተያየት

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ-ኢትዮጵያ

“በወዳጅነት እና በነጥብ የሚደረጉ ጨዋታዎች የጨዋታ ስልት እና ባህሪያቸው ይለያል፣ ተጋጣሚያችን በመጀመሪያው 20 እና 25 ደቂቃዎች ጉልበት የቀላቀለ ጨዋታ ሲጫወቱ ነበር። ኳስ ይዘን ለመጫወት በመቻላችን ጎሎች ማስቆጠር ችለናል።ወጣቶች ያስመዘገቡት ውጤት ከበቂ በላይ ነው በቀጣይ ችግሮቻችንን ቀርፈን እንሄዳለን።”

አሰልጣኝ መሀመድ ፈርኸያል -ሱማሊያ ብሔራዊ ቡድን

“ይሔ እግርኳስ ነው ጨዋታው በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቋል። የተሰጠብን ፍፁም ቅጣት ምት እና ከጨዋታው ቅደመ ጨዋታ በፊት የተባሉ ሁለት የአቡላንስ አግልግሎት አልተሟሉም። እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከተፈቀደው እድሜ በላይ ናቸው። ቡድናችን የልምድ እንጂ የክህሎት ችግር የለብንም።”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...