መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ኢትዮ- ኤሌክትሪክ አሰልጣኙን ባሰናበተ ማግስት የመጀመሪያ ድሉን ኢትዮጵያ ቡና ላይ አስመዘገበ፡፡
ሪፖርትኢትዮ-ኤሌክትሪክኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ኢትዮ- ኤሌክትሪክ አሰልጣኙን ባሰናበተ ማግስት የመጀመሪያ ድሉን ኢትዮጵያ ቡና ላይ አስመዘገበ፡፡

አጋራ
አጋራ

በኢትየጵያ ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ሳምንት ላይ መደረግ እያለበት በቻን ማጣሪያ ምክንያት የቀን ለውጥ ተደርጎበት በዛሬው እለት  የተከናወነው መርሃ ግብር በኢትዮ-ኤሌክትሪክ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ልክ 11:32 ደቂቃ ላይ የተጀመረው ጨዋታ በ የመጀመሪያው አጋማሽ 10ደቂቃ በኳስ ቁጥጥርና ወደ ጎል በመድረሱ ረገድ ኢት.ቡና የተሻሉ ሲሆን ከ10ኛው ደቂቃ በኋላ ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች ወደ ጨዋታው ለመመለስ ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። ይህንንም ተከትሎ 15ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮ-ኤሌክትሪኩ ቢኒያም አሰፋ ከቀኝ መሠመር የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮት የኢትዮጵያ ቡናው ግብ ጠባቂ ሀሪስተን በቀላሉ ይዟታል፡፡ በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረት ያደረጉት ኢትዮጵያ ቡናዎች 20ኛው እና 25ኛው ደቂቃ ላይ በአስቻለው ግርማ የሞከራቸው ኳሶች ወደ ውጭ ወጥተዋል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 8ደቂቃዎች ሲቀሩት 37ኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮ-ኤሌክትሪኩ አልሀሰን ካሉሻ ከግራ መስመር ያገኛትን ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ ጋር አገናኝቷት ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ይህች ግብ ከመሀል ሜዳ እየተነሳ ለሚጫወተው አልሀሰን ካሉሻ በሊጉ 6ኛ ጎሉ ሆና ተመዝግባለች።  ከግቧ መቆጠር በኃላ በኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ተቃውሞ የቀጠለው ጨዋታ ይሄ ነው የሚባል የረባ እንቅስቃሴ ሳይስተዋልበት የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል።

በሁለተኛው አጋማሽ ተሻሽለው መቅረብ የቻሉት ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች ጫና ፈጥረው በመጫወት ተጨማሪ ግቦችን ለማስቆጠር ጥረት ሲያደርጉ አምሽተዋል። 53ኛው ደቂቃ ላይ ቢኒያም አሰፋ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ አግኝቶ የሞከራትን ኳስ ግብ ጠባቂው ሀሪሰትን በቀላሉ ይዞታል፡፡ ከዚህ ሙከራ 5 ደቂቃዎች በኋላ 58ኛው ደቂቃ ላይ አወት ገ/ሚካኤል ያሻገረውን ኳስ ግርማ በቀለ አስቆጥሮ ቡድኑን 2-0 እንዲመራ አስችሎታል፡፡  ከግቧ መቆጠር በኃላም ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ቡና ግብ ክልል መድረስ የቻሉ ቢሆንም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።

ከሁለተኛው ግብ መቆጠር በኋላ ግብ ለማስቆጠር ጥረት ያደረጉት ኢትዮጵያ ቡናዎች 73ኛ ደቂቃ ላይ እያሱ ታምሩ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ አስቆጥሮ 2-1 ማድረግ ችሏል፡፡ ከግቧ  መቆጠር በኃላ ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች ውጤቱን ለማስጠበቅ አፈግፍገው ሲጫወቱ ኢትዮጵያ ቡናዎች በአንፃሩ አቻ የምታደርጋቸውን ግብ ለማግኘት በአስራት ቱንጆ  እና በእያሱ ታምሩ ጫና ፈጥረው ተጫውተዋል። ሆኖም ጨዋታው ተጨማሪ ግብ ሳይስተናገድበት በኢትዮ-ኤሌክትሪክ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ይህንን ውጤት ተከትሎም ኢትዮ-ኤሌክትሪክ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው 8ነጥቦችን ሰብስቦ 3 ደረጃዎችን በማሻሻል 12ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ኢትዮጵያ ቡና በአንፃሩ ከ8 ጨዋታዎች 11 ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰብ 7ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

የኮከብ ግብ አግቢነቱን በዛሬው ጨዋታ 1ግብ ያስቆጠረው የኢትዮ-ኤሌክትሪኩ አልሀሰን ካሉሻ እና የጅማ አባጅፋሩ ናይጄሪያዊ አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በእኩል 6ግቦች ሲመሩት የደደቢቱ አቤል ያለው በ5 ግቦች ይከተላል።
የአሰልጣኞች አስተያየት 

ጊዚያዊ የኢትዮ-ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ ቅጣው ሙሉ

“እስከ ዛሬ ድረስ የበረኛ አሰልጣኝ ሆኜ ቡዱኑን አሰልጥኛለሁ፡፡ዛሬ እድለኛ  ሆኜ  በዋና አሰልጣኝነት ቡድኑን እየመራሁ በማሸነፌ በጣም  ተደስቻለሁ፡፡ በጨዋታው ሙሉ 90 ደቂቃ በልጠን ነበር ያገኘናቸውን የጎል አጋጣሚዎች ተጠቅመን  አሸንፈን ወጥተናል፡፡”

ዲዲየ ጎሜዝ -ኢትዮጵያ ቡና

” በዛሬው የቡድኔ አቋም ተከፍቻለሁ፡ ቡዱኑን ከያዝኩ 6ቀኔ ነው ፡፡ ግዜ ያስፈልገናል ፍልስፍናዬን ተግባራዊ ለማድረግ እንሰራለን፡፡ በደጋፊው ደስተኛ ነኝ  በውጤት ባናስደስታቸው፡ በቀጣይ ያሉብንን ችግሮች ቀርፈን ወደ፡አሸናፊነት እንመለሳለን፡፡”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ድንቅ የቅጣት ምቶች በነበሩት ጨዋታ ነገሌ ሲያሸንፍ ሀዋሳ በወልዋሎ ነጥብ ጥሏል

7 ጎሎች እና ሁለት ድንቅ የቅጣት ምት ጎሎች በነበሯቸው ሁለት ጨዋታዎች ነገሌ...