መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ባህርዳር ከተማና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ አቻ ተለያይተዋል
ሪፖርትባህርዳር ከተማወልዋሎየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ባህርዳር ከተማና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ አቻ ተለያይተዋል

አጋራ
አጋራ

 

ባህርዳር ከነማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ አቻ ተለያይተዋ

የ26ኛው ሳምንት እሁድ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ባህርዳር ላይ ባህርዳር ከነማ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።ባህርዳር ከነማ በ25ኛው ሳምንት በ ደደቢት ከተሸነፈው ቡድን 7 ቅያሬዎችን ማለትም ሃሪሰን ሄሱን በምንተስኖት አሎ፣ሄኖክ አቻምየለህን በ አቤል ውዱ፣አሌክስ አሙዙን በወንድሜነህ ደረጀ፣ሚካኤል ዳትኛቸውን በዳንኤል ሃይሉ፣ዜናው ፈረደን በፍቃዱ ግርማ፣ጃኮ አራፋትን በልደቱ ለማ፣ወሰኑ አሊን በእንዳለ ደባልቄ ሲቀይሩ ውልዋሎዎች በበኩላቸው ካለፈው ሳምንት ስብስብ ምንም ቅያሬዎችን ሳያደርጉ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት።

የባህርዳር ከነማ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ አጋማሽ በ4-3-3 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት የጣና ፈርጦች በተሻለ መልኩ ወደ ግብ ቀርበዋል።በተለይ በእግራ መስመር በሚነሱ ኳሶች ባህርዳሮች የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።በ3ተኛው ደቂቃ አስናቀ ሞገስ ያሻማውን ልደቱ ለማ ሳይጠቀምበት ቀርቱዋል፡፡እንዲሁም በ 8ተኛው ደቂቃ በቀኝ በኩል የተሻማውን ኳስ ፍቃዱ ግርማ በቲቴስታ የሞከረው ኳስ ተጠቃሽ ነው።በ13ተኛው ደቂቃ በእለቱ አሪፍ ሲንቀሳቀስ የነበረው አስናቀ ሞገስ የሞከረው እና በግቡ ቋሚ አድርጎ የወጣው አሪፍ አጋጣሚ ነበር።በተለይ በ በ 38ተኛው ደቂቃ እራሱ ተጠልፎ ያገኘውን ቅጣት ምት ዳንኤል ሃይሉ የሞከረው በጣም አስቆጭ ሙከራ ነበር፡፡

በሁለተኛው አጋማሽ ውልዋሎ የተሻሉ ነበሩ።በ 47፣68፣82ተኛው ደቂቃ የሞከሩዋቸው ተጠቃሾች ናቸው።በተለይ በ 68ተኛው ደቂቃ አጥቂው ብቻውን ከ በረኛው ጋር ተገናኝቶ ወደላይ የሰደደው ውልዋሎዎች ካገኙት አጋጣሚዎች በጣም የሚያናድድ እና የሚያስቆጭ ነበር።በመጨረሻም ሁለቱም ቡድኖች ሳይሸናነፉ ጭዋታቸውን ያለምንም ጎል በ አቻነት ጨርሰዋል።

በአጠቃላይ ጭዋታው ምንም እንኩዋን ምንም ጎል ባይቆጠርበትም ተመልካችን ቁጭ ብድግ ያደረገና ፍጹም ጨዋነት የተሞላበት በጣም የሚያምር ጭዋታ ነበር፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ባህርዳር ከነማ ነጥቡን ወደ 37 በማሳደግ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ወልዋሎ በ አንጻሩ 36 ነጥብ በመያዝ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...