በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 24ተኛ ሳምንት ጨዋታ ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና አዳማ ከተማን አስተናግዶ በአዲስ ግደይ ብቸኛ የፍፁም ቅጣት ምት ግብ 1-0 በሆነ ጠባብ ውጤት አሸንፏል፡፡
በየኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር ታጅቦ በሰአቱ ዘጠኝ ሰአት ሲል በተጀመረው ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ደቂቃዎች ይሄነው የሜዳ ላይ የኳስ ያልታየበት የመጀመሪያው አጋማሽ ነበር።
በእንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች የመጀመሪያው የጨዋታ የመጀመሪያ የጨዋታ ክፍል ግዜ ደቂቃዎች በረጅሙ በሚጣሉ ኳሶች ዳዋ ሆቴሳ ሁለት ያልተሳኩ አጋጣሚዎችን አግኝቶ በቀላሉ ያመከነበት አጋጣሚ ነበር።
በ15ኛ ደቂቃ ላይ እንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች በበረከት ደስታ እና ሱራፌል ዳኛቸው አማካኝነት ሰብሮ ለመግባት ጥረት ሲያደርጉ ቢስተዋልም የሲዳማ ተከላካዮች በተለይ ፈቱዲን ጀማል ጥረት መክነዋል።
በ40ኛው ደቂቃ ላይ ሱራፌል ዳኛቸው በጥሩ የኳስ ቅብብል ከበረከት ጋር አድርጎ በመጨረሻም በረከት ደስታ አክርሮ ወደ ግብ መቷት ግብ ጠባቂው መሳይ አያኖ ሲያድንበት በ42ተኛው ደቂቃ ላይ ደግሞ አዲስ ግደይ ሁለት የአዳማ ተጫዋቾችን በማለፍም ከሙጂብ ቃሲም እግር ስር ነጥቆ ከግብ ጠባቂው ጃኮ ፔንዜ ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የመታትን ኳስ ጃኮ ፔንዜ አድኖበታል። የመጀመሪያው አጋማሽ በዚሁ ወደ መልበሻ አምርቷል።

ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከመጀመሪያው አጋማሽ በተሻለ መልኩ ሲዳማ ቡናዎች የተሻለ የማጥቃት ሂደት የታየበት ሲሆን በ53ኛው ደቂቃ ላይ ወንድሜነህ አይናለም ከርቀት አክርሮ መቷት ጃኮ ፔንዜ እንደምንም ያዳነበት በተቃራኒው እንግዳዎቹ አዳማ ከተማዎች ደግሞ 56ተኛው ደቂቃ ላይ ከነዓን ማርክነህ በግል ጥረቱ እየገፋ ገብቶ ያገኘውን እድልን በቀላሉ ሳይጠቀምቀት ያመከናት ኳስ እምታስቆጭ ነበረች። በ74ኛ ደቂቃ ላይ በመስመር ላይ በተደጋጋሚ የአዳማን ተከላካይ ሲረብሽ የነበረው አዲስ ግደይ በግራ በኩል እየገፋ ወደ ሳጥን ሲገባ በግብ ክልል ውስጥ በሙጂብ ቃሲም በመጠለፉ ምክንያት የእለቱ ፌዴራል ዳኛ ተካልኝ ለማ የሰጡትን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ አዲስ ግደይ በመምታት አስቆጥሮ የሲዳማን ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስጨብጧል።

ከግቡ መቆጠር በኃላም ይገዙ ቦጋለ እና አዲስ ግደይ እንዲሁም በወንድሜነህ አይናለም አማካይነት በርካታ የግብ እድልን ቢያገኙም ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ጫዋታው በሲዳማ ቡና 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል ፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ዘርአይ ሙሉ – ሲዳማ ቡና
“የዛሬው ጨዋታው ከባድ ነበር። ምክንያቱም ተጋጣሚያችን ይዞ የመጣሁ አጨዋወት ትንሽ ፈትኖን ነበር። በጨዋታው ባናሸንፍም ከስጋት እንወጣለን ልጆቼ አቅም አላቸው በቀጣይ ቡድናችንን ወደ ተፎካካሪነት እናመጣዋለን”
አሰልጣኝ ተገኔ ነጋሽ ~ አዳማ ከተማ
የጨዋታ ድህረ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል
አስተያየት ይስጡ