ምንይሉ ወንድሙ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

 

የጅማ አባጅፋር ደጋፊዎች ኃላፊነታችንን እንወጣ በማለት የእጅ ማስታጠብ እና ለአቅመ ደካሞች መለገስ የጀመሩት በጎ ተግባር ተጠናክሮ እየቀጠለ ይገኛል።

ለመከላከያ እግር ኳስ ክለብ እየተጫወተ የሚገኝው ምንይሉ ወንድሙ በጅማ ከተማ እና አካባቢ ስርጭቱን ለመከላከል ለሚደረጉ ተግባራት እና ለአቅመ ደካሞች የንፁህና መጠበቂያ ግዢ የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ለደጋፊው ማኀበሩ አድርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ይህን በጎ ተግባር ለማገዝ የሚፈልጉ ሌሎች የማኅበሩ አባላት እና የስፖርት ቤተሰቦች ማኅበሩ ባዘጋጀው የባንክ አካውንት መለገስ የሚችሉ መሆኑን ማኅበሩ አስታውቋል።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer