በዘንድሮው የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እሚገኘው መቐለ ከተማ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ካስፈረማቸው 3 አዲስ ተጫዋቾችና ከሁለት ነባር ተጫዋቾች ጋር በስምምነት ክለቡ አሰናብቷቸዋል ።
ከተሰናበቱት ተጫዋቾች መካከል ዱላ ሙላቱ(ከሀዲያ ሆሳዕና የፈረመ) ፣ዮሱፍ ደንገቶ (ከወላይታ ድቻ የፈረመ)፣ሙሉጌታ ረጋሳ (ከወልዲያ የፈረመ)፣ዮሴፍ ሀይሉ (ነባር )፣ ተመስገን አዳሙ (ነባር) ከነዚህ ተጫዋቾች ጋር የ3ወር ደሞዝ በመክፈል በስምምነት መለያየቱ ክለቡ ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ አስታውቋል።
ክለቡ አምስቱን ተጫዋቾች ለማሰናበት የተገደደው እሚፈለገውን ግልጋሎት ሊሰጡት ባለመቻላቸው መሆኑን አያይዞ ገልጿል።
መቐለ ከተማ በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ እየተመራ ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች በስድስት ጨዋታ ድል ሲቀናው በስድስት ጨዋታ በአቻ ውጤት አጠናቆ በአንድ ጨዋታ ብቻ ሽንፈት አስተናግዶ ከመሪው ደደቢት በአንድ ነጥብ ተበልጦ በ24 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
አስተያየት ይስጡ