ሀትሪክ አበይት | የ17ኛ ሳምንት ዋና ዋና ጉዳዮች

👉👉 ተጠባቂው ጨዋታ ያለግብ ተጠናቋል።

👉👉ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ አመት ለመጀመሪያ ግዜ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ሸንፈት አስተናግዷል።

👉👉አዳማ ከተማ በአመቱ የመጀመሪያውን የሜዳ ውጭ ድል አሳክቷል።

👉👉ሙጂብ ቃሲም ለተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ግብ ሳያስቆጥር ወጥቷል።

👉👉ሳልሀዲን ሰይድ በደጋፊዎች ጥቃት ደርሶበታል

👉👉ግቦች

👉👉ውጤቶች

👉👉የደረጃ ሰንጠረዥ

👉👉ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች

 

ተጠባቂው ጨዋታ ያለግብ ተጠናቋል።

አርብ ትግራይ ስታዲዮም ላይ የተደረገው የመቐለ 70 እንደርታ እና ባህርዳር ከነማ ጨዋታ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል። የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች ክለባቸውን ለመደገፍ ወደ መቐለ ሲገቡ በመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ደማቅ አቀበባል የተደረገላቸው ሲሆን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላም የእራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል። ይህ የደጋፊዎች ሰላማዊ መንፈስ ለእግር ኳሱ መልካም ገፅታ ከመፍጠር አኳያ ሊበረታታ የሚገባው ነው።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚህ አመት ለመጀመሪያ ግዜ በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ሸንፈት አስተናግዷል።

ዋና አሰልጣኙን እና ረዳቶችን ማገዱን ተከትሎ በሲኒየር ተጫዋቾች እየተመሩ ጨዋታውን ያደረጉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች 34ኛው ደቂቃ ላይ አስቻለው ግርማ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሸንፈት አስተናግደዋል። ከሳምንት በፊት ፈረሰኞቹ በወልቂጤ ከተማ ሽንፈት አስተናግደው እንደነበር የሚታወስ ነው።

አዳማ ከተማ በአመቱ የመጀመሪያውን የሜዳ ውጭ ድል አሳክቷል።

በፌደሬሽኑ በተጣለበት ቅጣት ምክንያት ሁለት ጨዋታዎችን ከሜዳው ውጭ እንዲያደርግ የተወሰነበት ወልቂጤ ከተማ በአዳማ ከተማ 2-0 ሽንፈት ቀምሷል። ወልቂጤ ላይ ድል የተቀዳጁት አዳማ ከተማዎች በዚህ አመት ከሜዳቸው ውጭ ያሳኩት የመጀመሪያው ሶስት ነጥብ ሆኗል። ለአዳማ ከተማ ከነዓን ማርክነህ እና በረከት ደስታ የማሸነፍያውን ግብ ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

5 ጨዋታዎች በአመቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል።

በዚህ ሳምንት ከተደረጉት 8 ጨዋታዎች አምስቱ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል። ይህ ደግሞ በሊጉ የ17 ሳምንታት ጉዞ በ1ሳምንት ጨዋታዎች በርካታ የአቻ ውጤቶች የተመዘገበበት ሳምንት ያደርገዋል።

ሙጂብ ቃሲም ለተከታታይ ሶስት ጨዋታ ግብ ሳያስቅጥር ወጥቷል።

የፋሲል ከነማው አጥቂ እና ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን በ14 ግቦች በመምራት ላይ የሚገኘው ሙጂብ ቃሲም ለተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ግብ ሳያስቆጥር ወጥቷል። በ14ኛው ሳምንት አፄዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊስን አስተናግደው 2-2 በተለያዩበት ጨዋታ ግብ ያስቆጠረው አጥቂው ባለፉት ሳምንታት ግብ ማስቆጠር ተስኖታል።

ሰልሀዲን ሰይድ በደጋፊዎች ጥቃት ደርሶበታል

ፈረሰኞቹ ሽንፈት ካስተናገዱበት የሰበታ ጨዋታ በኋላ ሁለት የክለቡ ደጋፊዎች የፊት መስመር አጥቂውን መትተውታል። ተጫዋቹ 62ኛው ደቂቃ ላይ በእለቱ ዳኛ ከሜዳ በቀይ ካርድ የተወገደ ሲሆን በቀይ ካርዱ የተበሳጨው ተጫዋቹም በደጋፊዎቹ ከተመታ በኋላ ክቡር ትሪቡን አካባቢ የሚገኘውን መስኮት በስሜታዊነት መትቶ ጉዳት አስተናግዶ ወደ ቤተዛታ ሆስፒታል ተወስዶ የህክምና እርዳታ ተደርጎለት ማምሻውን ወጥቷል።

ግቦች

በ 17ኛ ሳምንት 10 ግቦች ተቆጥረዋል። ይህ ማለት ደግሞ 1.25 በአማካይ ተቆጥረዋል ማለት ነው። ባለፈው ሳምንት ከተቆጠሩ ግቦች ደግሞ በ17 ዝቅ ብለዋል። የተቆጠሩት ሁሉም 10 ግቦች በተለያዩ ተጫዋቾች የተቆጠሩ ሲሆን የአዳማ ከተማው ከነዓን ማርክነህ 5ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠረው ግብ ፈጣኑ ሲሆን የጅማ አባጅፋር ኤርሚያስ ሀይሉ 90ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ በሳምንቱ ዘግይታ የተቆጠረች ግብ ሆናለች።

ውጤቶችና የደረጃ ሰንጠረዥ

በሳምንቱ ከተደረጉት 8 ጨዋታዎች 5ቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ ቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቀዋል። በሳምንቱ የተደረጉት የጨዋታ ውጤቶች እንደሚከተለው በፎቶ አስቀምጠናል።

ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች

የፋሲል ከነማው አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በ14 ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሲመራው ሀብታሙ ገዛኸኝ እና አዲስ ግደይ ከሲዳማ ቡና፣ ብሩክ በየነ ከሀዋሳ ከተማ፣ ፍፁም አለሙ ከባህርዳር ከነማ እና ባየ ገዛኸኝ ከወላይታ ድቻ በእኩል 9 ግብ ይከተላሉ።

Hatricksport website writer

ዳዊት ታደሰ

Hatricksport website writer