ሀትሪክ ስፖርት በነገው እትሟ
የመጀመሪያዋ ባለቀለምና ተወዳጇ ሀትሪክ ሳምንታዊ የስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን አካታ ነገ ማለዳ እጅዎ ትገባለች ይጠብቋት ።
ሀትሪክ ምን ምንን ጉዳዬችን ይዛ ወጥታ ይሆን? በሀገር ውስጥ THE BIG iNTERVIEW በሚለው አምድ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሙሉዓለም መስፍን ዴኮ በክለቡና በራሱ የኳስ ህይወት ዙሪያ ይናገራል። ተጨዋቹ ምን ብሎ ይሆን?
ሀትሪክ በሌላ ዘገባዋም በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ድራማቲክ ውጤት ስለተመዘገበበት የሰበታ ከተማና የፋሲል ከነማ ግጥሚያ የሁለቱ ቡድን ተጨዋቾች ፍፁም ገብረ ማሪያም እና ሽመልስ ጉግሳ የሚሉትን አቅርበንሎታል።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ ለሊጉ መሪ ሊቨርፑል ጎሎች መቆጠር ምክንያት ስለሆነው አሌክስአንደር አርኖልድ እንደዚሁም ስለ አርሰናሉ ኦባምያንግ ስለ ማንቸስተር ዩናይትዱ አንቶኒዬ ማርሽያል እና ሌሎችንም ምርጥ ምርጥ መረጃዎችን ይዛሎት ቀርባለች።
የነገ ሀትሪክ ጋዜጣዎ አታምልጦት።
ሀትሪክን ከጋዜጣዋ በተጨማሪ ከፍተኛ መሻሻል ባሳየውና በአጭር ጊዜ በርካታ ጎብኚዎች ባሉት በድረ-ገፅዋ hatricksport.net አዳዲስ መረጃዎችን ያገኛሉና ዛሬውኑ ይጎብኙን።
ሀትሪክ አ
የሀትሪክ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።
አስተያየት ይስጡ