መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጅማ አባቡና ያቀረበውን ክስ በተመለከተ ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጅማ አባቡና ያቀረበውን ክስ በተመለከተ ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 30 ኛ ሳምንት ሰኔ 17 2009 ዓ/ም ከተደረጉ ጨዋታዎች መካከል በሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮ ኤሌትሪክ በተደረገው ጨዋታ የውጤት ማስለወጥ ሙከራ ተደርጓል ሲል የጅማ አባቡና እግር ኳስ ቡድን ባስገባው የክስ አቤቱታ ፌዴሬሽኑ ነገ በ10 ሰዓት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ውሳኔውን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ለስፖርት መገናኛ ብዙሐን በላከው ኢሜል መልዕክት አስታውቋል ፡፡

ፈዴሬሽኑ ለመገናኛ ብዙሐን የላከው መልእክት 

ለሁሉም የስፖርት መገናኛ ብዙሃን

በ2009 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ዙር እግር ኳስ ውድድር በሀዋሳ ከነማ እና በኢትዮ ኤሌትሪክ መካከል ከተካሔደው ጨዋታ ጋር በተያያዘ ውጤት ለማስለወጥ የተደረገ ሙከራ “አለ” መባሉን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉዳዩን ተከታትሎና አጣርቶ ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲያቀርብ አንድ አጣሪ ቡድን አቋቁሞአል፣ በመሆኑም ቡድኑ አጣርቶ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በተመለከተ ሀሙስ ነሐሴ 04/2009 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት በኢንተርኮንትኔንተል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...