መነሻ ገጽ ኮንፌድሬሽን ካፕ ዜና | ዛማሌክ ትልቅ ቡድን መሆኑን ብናውቅም ከጨዋታው በፊት ግን አንሸነፍም።
ኮንፌድሬሽን ካፕወላይታ ድቻዜናዎች

ዜና | ዛማሌክ ትልቅ ቡድን መሆኑን ብናውቅም ከጨዋታው በፊት ግን አንሸነፍም።

አጋራ
አጋራ


የወላይታ ዱቻው አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ ከዚማማቶ ድላቸው በኀላ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ ገፅ ጋር አጭር ቆይታ!

ሀትሪክ፡- ጨዋታው እንዴት ነበር?

ዘነበ፡- ምንም እንኳን ከሜዳችን ውጪ ነጥብ ተጋርተን መመለሳችን መልካምቢሆንም የመልሱ ጨዋታም ቀላል እንደማይሆን እናውቀው ነበር፡፡
ያጋጠመንም ይሄው ነው፡፡ በሁለታችንም በኩል ከባድ ፉክክር አድርገናል፡፡ በመጨረሻም በውጤቱ ተደስተናል፡፡

ሀትሪክ፡- በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ ተወስዶባችኀል። ምክንያቱ ምንድነው?

ዘነበ፡- በዚህ ጉዳይ ከልጆቼ ጋር በእረፍት ሰአት ላይ ተነጋግረን ነበር፡፡ ነገር ግን ሜዳ ሲገቡ እኔ ካልኳቸው ውጪ መከላከልን ምርጫቸው አደረጉ። ይሄ ደግሞ የመሀል ክፍላችን እንዲከፈት አድርጎታል፡፡ ይሄንን ያደረጉት ውጤቱን አስጠብቀው ለመውጣት በመጓጓታቸው መሆኑን ነግረውኛል። የመጨረሻዎቹ 20 ደቂቃዎች ላይ ደግሞ የጉልበት መዳከም ተፈጥሮብናል፤ ይህን መካድ የለብንም፤ ብዙ መስራት አለብን፡፡

ሀትሪክ፦ መከላከልን ብቻ መሰረት ያደረገ አጨዋወት እስከመቼ ነው የምትዘልቁበት?

ዘነበ፦ ይሄ ክለቡ ውስጥ የቆየ ባህል ነው፤ ማስተካከል አለብን፤ አሁንም ቢሆን ለውጦች አሉ፤ ግን የበለጠ መስራት አለብን፤ በአጭር ጊዜ ለውጥ ታያላችሁ፡፡

ሀትሪክ-ከሳምንታት በኋላ በሚከፈተው የዝውውር መስኮት ተጫዋቾች ለማስፈረም አቅዳችኋል?

ዘነበ:-በዝውውር መስኮቱ ተጫዋቾችን እናስፈርማለን በተለይም ክፍተት ያሉብን ቦታዎችን ለመድፈን 4ያክል ተጫዋቾችን እናስፈርማለን።

ሀትሪክ፦ ስለ ቀጣይ ተጋጣሚያችሁ ዛማሌክ ምን ትላለህ?

ዘነበ፦ አዎ ተጋጣሚያችን በአፍሪካ የእግር ኳስ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያለው መሆኑን እናውቃለን፡፡ ይህ ማለት ግን ወቅታዊ አቋማቸውን ይገልፀዋል ማለት አይደለም፡፡ ድል አድርገን ታሪክ ለመስራት እንጥራለን፤ ከጨዋታው በፊት አንሸነፍም፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...