መነሻ ገጽ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ 29ኛው ሳምንት  የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የመውረድ ስጋት ያለባቸው ኢትዮ-ኢሌትሪክ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማሸነፋቸው ለያንዳንዱ  ተጫዋች ማበረታቻ የ10ሺ ብር ስጦታ ሰጠዋል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ 29ኛው ሳምንት  የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ የመውረድ ስጋት ያለባቸው ኢትዮ-ኢሌትሪክ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማሸነፋቸው ለያንዳንዱ  ተጫዋች ማበረታቻ የ10ሺ ብር ስጦታ ሰጠዋል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ  በ29ኛው ሳምንት ሶስተኛ ቀን  ጨዋታ መከላከያ እና አዳማ ከተማ ያለምንም ጎል ነጥብ ተጋርተዋል፡፡  10:30 እዲጫወቱ መርሃ ግብር ተይዞላቸው የነበረው የደደቢት እና ሲዳማ ቡና ጨዋታ ለረቡዕ ሰኔ 14 ቀን 2009 ዓ.ም  በ10:30 እዲጫወቱ ቀን ተቆርጦላቸዋል ፡፡

በ29ኛ ሳምንት በተደረጉ 7 ጨዋታዎች ፤ ላለመውረድ እሚደረጉ አጎጊ ትእይንቶች ቀጥለዋል፡
በ ሊጉ ትናንት  አምስት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።በመርሃ ግብሮች የመውረድ ስጋት የተደቀነባቸው ቡድኖች አሸናፊ መሆን ችለዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በከፍተኛ የደጋፊዎች ተቃውሞ በተደረገ  ጨዋታ ደግሞ፥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮጵያ ቡናን በቢኒያም አሰፋ በቢንያም አሰፋ  ሁለት ጎሎች በ በተመሳሳይ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ክልል ላይ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ድሬዳዋ ከተማን ያስተናገደው ፋሲል ከነማ ያለምንም ጎል ጨዋታውን በአቻ ውጤት አጠናቋል።

አርባ ምንጭ ላይ ወላይታ ዲቻን ያስተናገደው አርባ ምንጭ ከተማ ደግሞ በሜዳው በፈቱዲን ጀማል  ግብ የ1 ለ 0 ሽንፈትን አስተናግዷል።

በአዲስ አበባ ቃሊቲ መድን ሜዳ  ላይ ፖሊስ በሰዓቱ ባለመገኘቱ መጀመር ከነበረበት 40ደቀቃዎችን ዘግይቶ የተጀመረው  ጨዋታ  በመጀመሪያው አጋማሽ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በዳዊት እስጢፋኖስ   እና አዲስ ነጋሽ(ፍ.ቅ.ም) በተቆጠሩ ሁለት ጎሎች ወልዲያ ከተማን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።

ጅማ ላይ የተደረገው የጅማ አባ ቡና እና የሃዋሳ ከተማ ጨዋታበሃይደር ሸረፋ እና ሱራፈል አወል ሁለት ጎሎች በጅማ አባቡና 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ውጤቱን ተከትሎም ላለመውረድ የሚጫወቱ ቡድኖች ትንቅንቅ 30ኛ ሳምንትን ተጠባቂ አድርጎታል ።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ31፣ ድሬዳዋ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ 32 ነጥቦችን ይዘው የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታቸውን ይጠብቃሉ።

ደረጃ ሰንጠረዥ 

 


በ30ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ወላይታ ዲቻ፣ አርባ ምንጭ፣ ወልዲያ እና ሃዋሳ ከተማም በመጨረሻው ሳምንት ተሸንፈው ከታች ካሉ ቡድኖች አንዳቸው ማሸነፍ ከቻሉ ምናልባት አንደኛውን የወራጅ ኮታ የሚሞሉበት አጋጣሚ ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀይቆቹ የመጀመሪያ ድላቸውን ሲያሳኩ፣ ፈረሰኞቹም በድል የአምስተኛውን ሳምንት ጨዋታ አጠናቀቁ!

በአቤኔዘር አበበ ሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳኩ ሀዋሳ ከተማ...