መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ማሸነፍ ተስኖታል።
ሪፖርትአዳማ ከተማኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ሪፖርት | ኢትዮጵያ ቡና አሁንም ማሸነፍ ተስኖታል።

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት አንድ ጨዋታ አዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ ሲደረግ አዳማ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡናን አገናኝቶ በባለሜዳዎቹ አዳማ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ከጨዋታው መጀመር በፊት የአዳማ ከተማ ክለብ አስጨፋሪ አቻምየለህ (እሙጢሽ) የሰርግ ስነስረዓቱን በስታዲየሙ ውስጥ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ዜማ ታጅቦ ማከናወን ችሏል፡፡

በአዳማ ከተማ በኩል በ4-3-3 ቅርፅ ሲገቡ ተጋጣሚው ኢትዮጵያ ቡና በ4-5-1 አሰላለፍ ይዘው ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡

ጨዋታው በተጀመረ 3ኛው ደቂቃ ላይ በአዳማ ከተማ ተጨዋቾች ላይ በተሰራ ጥፋት የተገኘችውን ቅጣት ምት ዳዋ ሁቴሳ በግሩም ሁኔታ የግቡን ብረት ለትሞ ያስቆጠረው ኳስ አዳማ ከተማዎችን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ሆኖም ግን የአዳማ ከተማዎች መሪነት መዝለቅ የቻለው ለ3 ደቂቃዎች ብቻ ነበር። 6ኛው ደቂቃ ላይ መስዑድ መሀመድ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሳሙኤል ሳኑሚ በማስቆጠር ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡ ከጎልዋ መቆጠር በኃላ በሁለቱም ቡድኖች በክንፍ መስመር የሚጣሉ ኳሶች ነበሩ፡፡ 8ኛው ደቂቃ ላይ የአዳማ ከተማው ኤፍሬም ዘካሪያስ የመታትን ኳስ የኢትዮጵያ ቡናው ሀሪሰተን በቀላሉ ይዟታል። በጨዋታው ከአዳማ ከተማው ተጫዋች ኤፍሬም የሚነሱት ኳሶች ለባለሜዳዎቹ የማጥቃት መሰረት ነበሩ፡፡
የቀድሞ የቅ/ጊዮርጊስ ተጫዋች አንዳርጋቸው ይላቅ ከግምት 33ሜትር ከርቀት የሞከራት ኳስ በሀሪሰተን ጥረት ወደ ውጪ ወጥታለች። ከዚህች ሙከራ በተጨማሪ ይሄ ተጫዋች ወደ ኢት/ቡና ክልል የሚጥላችው ኳሶች አደጋ ሲፈጥሩ ተስተውሏል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 5ደቂቃዎች ሲቀሩት 40ኛው ደቂቃ ላይ ከመሀል የተሻገረለትን ኳስ የአዳማ ከተማው በረከት ደስታ አስቆጥሮ 2-1 እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል፡፡

በሁለተኛውም አጋማሽ አዳማ ከተማዎች አብላጫውን መውሰድ ችለው ነበር። 65ኛው ደቂቃ ላይ ዳዋ ሁቴሳ ጥፋት ተሰርቶበት የተሰጠውን ኳስ እራሱ መቶ ወደ ውጭ ወጥቶበታል፡፡ ከ2ደቂቃዎች በኋላ 67ኛው ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባው የአዳማ ከተማው አዲስ ነጋሽ ያገኘውን የጎል ማግባት አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
ከ70ኛው ደቂቃ በኋላ ጨዋታው እጅግ እየተቀዛቀዘ የሄደው ጨዋታ በአዳማ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የአሰልጣኞች አሰተያየት

አዳማ ከተማ -ተገኔ ነጋሽ
“በመጀመሪያ ፈጣሪን ማመስገን እፈልጋለሁ። በጨዋታው ሙሉ በ ሙሉ ልጆቼ ጥሩ ነበሩ፡፡በጉዳት የወጡብን ልጀች ቶሎ አገግመው ወደ ጨዋታ ይመለሳሉ ብለን ተስፋ እደርጋለን፡፡”

 መሀመድ ኢብራሂም  የኢት/ቡና ም/አሰልጣኝ
“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፤ ጥሩ ፉክክር አሳይተናል፡፡ አስበን ወደ ሜዳ የገባነውን መጫወት አልቻልንም፤ በተቆጠረብን ሁለት ጎሎች ተሸንፈናል። እንግዲህ አዲስ አሰልጣኞች ነን ቡድኑን አስተካክለን ወደ ቀድሞ ቦታችን ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን፡፡”

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡናና መቻል ያለ ግብ ስለያዩ፤ ወላይታ ድቻ ወልዋሎን በማሸነፈ የድል ጉዞውን ቀጥሏል!

በአቤኔዘር አበበ ሲዳማ ቡና ከመቻል ጋር ያለ ግብ ሲለያዩ፣ ወላይታ ድቻ ወልዋሎ...