*…እስካሁን ያዘዋወሩት ሁለት ክለቦች ብቻ ናቸው…
ላለፉት ሳምንታት ክፍት በነበረው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ሶስት ተጨዋቾች ብቻ መዘዋወራቸው ታውቋል።
ነገ ለሊት 6 ሰዓት በሚዘጋው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑ ባረጋገጠው ዝውውር
ፋሲል ከነማ ዱላ ሙላቱን ከጅማ አባጅፋር ሲያስፈርም ኢትዮ. ኤሌክትሪክም አማራ በቀለና አብዱራህማን ሙባረክን ከድሬድዋ ከነማ ሲያስፈርም የማታይ ሉልን ኮንትራት አድሷል። ውሉ ህጋዊ ባይሆንም ፋሲል ከነማን ለሊጉ ፍልሚያ እያዘጋጀ ያለው አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከዚህም በላይ ወጣቱን ተስፈኛ ዳንኤል ዘመዴን ማሰናበቱ ታውቋል።
- ማሰታውቂያ -
ከሊጉ 16 ክለቦች እስካሁን 14ቱን በተመለከተ ምንም ዝውውር አለመኖሩ ታውቋል። በ14ኛው ሳምንት መርሃግብር ሁለቱ ክለቦች ፋሲል ከነማና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚጫወቱ መሆኑ ታውቋል።