መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አዳማ ከተማ ዲሲፕሊን ጥሰዋል ያላቸውን ተጨዋቾች ቀጣ
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አዳማ ከተማ ዲሲፕሊን ጥሰዋል ያላቸውን ተጨዋቾች ቀጣ

አጋራ
አጋራ

አዳማ ከተማ የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽመዋል ቡድኑን ጎድተዋል ያላቸውን ስድስት ተጨዋቾቹን መቅጣቱ ታወቀ።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ የዲሲፕሊን ጥሰት ፈጽመዋል የአቋም መውረድ አሳይተዋል የተባሉ ስድስት ተጨዋችቹ ላይ ከአንድ ወር ደመወዛቸው 80 በመቶ ቅጣት በማስተላለፍ ሁለት ተጨዋቾቹ ላይ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ታውቋል።

ክለቡ በርካታ ወጣቶችን ወደ ቡድኑ በመቀላቀል ለአዳማ ከተማው ፍልሚያ የተዘጋጀ ቢሆንም ቅጣት የተላለፈባቸው ተጨዋቾች ስነምግባር ጥሰት ወጣቶቹን እንዳያበላሽ ክትትል እንደሚያደርግና ቀጣይ ርምጃ እንደሚወስድ ከታማኝ ምንጭ የተገኘው መረጃ ያስረዳል። የስድስት ተጨዋቾቹን ማንነት ምንጫችን ከመግለጽ ቢቆጠብም በቀጣይ የተጫዋቾቹን ዝርዝር የምናሳውቅ ይሆናል።
በዲሲፕሊን ላይ አይደራደርም የሚባልለት አሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ በ2014 ዲሲፕሊን ጥሰዋል በሚል ሁለት ተጨዋቾችን ከቡድኑ ማባረሩ ይታወሳል።

በአዳማ ከተሚ ለሚካሄደው ውድድር ዝግጅቱን እያደረገ ያለው አዳማ ከተማ በ14ኛ ሳምንት መርሃግብር ከኢትዮጵያ መድን ጋር ይገናኛል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...