በድንቅ ጉዞ ላይ የሚገኙት ሀድያ ሆሳዕናዎች ያደረጓቸውን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፊ የሊጉ መሪነት ላይ ያቆናጠጣቸውን ውጤት በጥቂት ደጋፊዎቻቸው ደማቅ ዝማሬ ታጅበው ሲዳማ ቡናን በመርታት ድል ተቀዳጅተዋል ።
በበርካታ ሙከራዎች በታጀበው የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች አል ሀሰን ካሉሻ ሞክሮት የግቡ አግዳሚ የመለሰበት ሙከራ የመጀመሪያው የግብ ሙከራ ነበር ። ሀድያ ሆሳዕናዎች ከደቂቃዎች በኋላ ሙከራቸው ፍሬ አፍርቶላቸው ሄኖክ አርፊጮ ያሻማውን የማዕዘን ምት ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ፕርሚየር ሊጉ የተመለሰው አይሳክ ኢሴንዴ ሀድያዎችን ቀዳሚ አድርጓል ።
- ማሰታውቂያ -
ሲዳማ ቡናዎች ከግቡ መቆጠር በኋላ በኋላ በ አዲስ ቱላ እንዲሁም ሀብታሙ ገዛኸኝ ሙከራዎችን ቢያደርጉም በሀድያ ሆሳዕና ግብ ጠባቂ መሀመድ ሙንታሪ ሊድን ችሏል ።
የመጀመሪያው አጋማሽ በዚህ መልኩ ሲጠናቀቅ የሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ ሀድያ ሆሳዕናዎች መሪነታቸውን ያሳፉበትን ግብ ቢስማርክ አፒያ በማስቆጠር የግብ መጠኑን ወደ ሁለት ከፍ አድርጎታል ።
ከደቂቃዎች በኋላ ሀድያዎች ተጨማሪ ጎልን ሲያስቆጥሩ ሌላኛው የፊት መስመር ተጫዋች ሳሊፍ ፎፎና የግል ብቃቱን በመጠቀም ለሀድያ ሆሳዕናዎች ሶስተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል ።
ሲዳማ ቡናማዎች የማጥቃት አማራጫቸውን በማስፋት ወደ ግብ ቶሎ ቶሎ ለመድረስ ቢሞክሩም እምብዛም የተሳካ ሆኖ አልታየም ። ወደ ጨዋታው መገባደጃ ላይ ከቆሙ ኳስ የተገኘውን ኳስ የሲዳማው የመሀል ተከላካይ ጊትጋት ኮች ወደ ግብነት ሲቀይር የግቡን መቆጠር ተከትሎ በተፈጠረ መጠነኛ ግጭት ሀድያ ሆሳዕናዎች ግብ ጠባቂያቸውን መሀመድ ሙንታሪን በቀይ ካርድ ለማጣት ተገደዋል ።
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕናዎች ያደረጉትን ሶስት ጨዋታዎች በማሸነፍ የሊጉ አናት ላይ መቀመጥ ችለዋል ።