ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 3ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።
የፕሪሚየር ሊጉ የድሬዳዋ የመጨረሻ ቆይታ በሆነዉ ሀያ ሁለተኛዉ ሳምንት የመጀመሪያ ዕለት ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን 3ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።
በዋና ዳኛ ሄኖክ አበበ መሪነት በጀመረዉ የዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ሁለቱም ክለቦች ከሚገኙበት የወራጅ ቀጠና ስጋት ለመዉጣት ከሚያደርጉት ጥረት አንፃር ጨዋታዉን እጅግ በጥንቃቄ ለመከዉን ሲጥሩ የተስተዋለ ሲሆን ፤ በመርሐግብሩም ገና በመባቻዉ በ4ተኛዉ ደቂቃ ላይ ወልቂጤ ከተማዎች በፋዓድ አብደላ አማካኝነት ሙከራ ቢያደርጉም ኳሷ የግቡን ቋሚ ገጭታ ወጥታለች።
- ማሰታውቂያ -
በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚ ቡድን የግብ ክልል መድረስ የቻሉት እና በኳስ ቁጥጥሩ ረገድም መጠነኛ ብልጫ የነበራቸዉ ወልቂጤ ከተማዎች እንደነበራቸዉ ብልጫ ግን የግብ ዕድል ለመፍጠር ሲቸገሩ ተስተውሏል። በተቃራኒው በሂደት ወደ ጨዋታዉ መመለስ የቻሉት መድኖች በጄሮም ፍሊፕ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ቢያደርጉም በተመሳሳይ የግቡ ቋሚ ኳሷን መልሷታል።
በድጋሚ ከኋላ ክፍል ሚሊዮን ሰለሞን በረዥሙ የጣለለትን ኳስ ብሩክ ሙሉጌታ ኳሷን ለማግኘት የጣረ ቢሆንም የገር ግን የግብ ዘቡ ፋሪስ በቅልጥፍና ኳሷን ተቆጣጥሯል። በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታ ላይም በ39ነኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ተቆጥሯል ። በዚህም አቡበከር ሳኒ ወደ ሳጥን ያሻገረዉን ኳስ አጥቂዉ ጄሮም ፍሊፕ በግንባሩ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን ኢትዮጵያ መድን መሪ ማድረግ ችሏል።
በሁለተኛዉ አጋማሽ ተሻሽለዉ የተመለሱት ኢትዮጵያ መድኖች በሁለቱም መስመሮች በኩል ጫናን ፈጥረዉ ለመጫወት ሲሞክሩ በተለይ በፊት መስመር ተጫዋቾቹ ጀሮም ፍሊፕ እና አቡበከር ሳኒ አማካኝነት ጥሩ ጥሩ ዕድሎችን መፍጠር ችለዋል።
በ52ተኛዉ ደቂቃ ላይ ብሩክ ሙሉጌታ በጫና የተገኘን ኳስ በቀጥታ ወደ በግብ በመሞክርም እና በተጨማሪም 58ተኛዉ ደቂቃ ላይ ደግሞ አቡበከር ሳኒ ጥሩ ሙከራ ቢያደርጉም የግብ ዘቡ ፉሪስ ግን ኳሶቹን አምክኗል። ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር የተቀዛቀዘ የጨዋታ ጊዜ እያሳለፉ የቀጠሉት ክትፎዎቹ በ80ኛዉ ደቂቃ ላይ ተጨማሪ ግብ አስተናግደዋል። በዚህም አቡበከር ሳኒ ከቡድን አጋሮቹ የተቀበለዉን ኳስ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ያቀበለዉን ኳስ ወገኔ ገዛኸኝ ሁለተኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።
በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም በዘጠናኛዉ ደቂቃ ላይ በዕለቱ ድንቅ መንቀሳቀስ የቻለዉ አቡበከር ሳኒ አስደናቂ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታዉን 3ለ0 በሆነ ዉጤት ኢትዮጵያ መድን ወልቂጤ ከተማን ማሸነፍ ችሏል።
ባህርዳር ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸዉን ያለ ግብ በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል ።
ምሽት አንድ ሰዓት ሲል በርከት ባሉ የደጋፊዎች ድባብ ታጅቦ መከናወን በጀመረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ገና በጊዜ የሀድያዉ ተከላካይ በረከት ቸርነት ጉግሳ ላይ ጥፋት መስራቱን ተከትሎ የተሰጠዉን የፍፁም ቅጣት ምት ራሱ ቸርነት ጉግሳ ቢመታም ነገር ግን ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል ።
በተመጣጣኝ የጨዋታ እንቅስቃሴ ድንቅ ፉክክርን እያስመለከተን በቀጠለዉ መርሐግብር በ ደቂቃ ላዮ ሀድያዎች ከመስመር በኩል በረከት ያሻገረውን ኳስ የመስመር ተጫዋቹ በየነ ባንጃዉ ሳጥን ዉስጥ በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክርም ኳሷ በግቡ አናት ላይ ወደ ዉጭ ወጥታለች።
በይበልጥ ወደ ግራ ባመዘነ የጨዋታ እንቅስቃሴ ጫና ፈጥረዉ መጫወታቸዉን የቀጠሉት የጣና ሞገዶቹ በ43ተኛዉ ደቂቃ ላይ የመስመር ተከላካዩ ፍራኦል መንግስቱ ከግራ መስመር በኩል በቀጥታ ወደ ግብ የሞከረዉ ኳስ ወደ ዉጭ ወጥቷል ።
ከዚች የጣና ሞገዶቹ ሙከራ በኋላም ሀድያ ሆሳዕናዎች ከቅጣት ምት በዳዋ ሁቴሳ አማካኝነት በቀጥታ ድንቅ ሙከራ አድርገዉ የነበረ ቢሆንም ኳሷን የግብ ዘቡ ፔፔ ተቆጣጥሯታል። በጨዋታዉ መሐልም አጥቂዉ ሙጅብ ቃሲም የትከሻ ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ ወጥቷል ።
ከዕረፍት መልስ አባይነህ ፌኖ ከቸርነት ጉግሳ የተቀበለዉን ኳስ ከኋላዉ ለሚገኘዉ ፍቅረሚካኤል አለሙ አቀብሎት የነበረ ሲሆን ተጫዋቹም ኳሷን በቀጥታ ወደ ግብ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በግቡ አናት ላይ ወጥታለች።
በ71ኛዉ ደቂቃ ላይ ግብ ጠባቂዉ ፔፔ በረዥሙ ሊመታ የነበረዉን ኳስ አጥቂዉ ዳዋ ሁቴሳ ተደርቦ ብሎክ አድርጎበት የነበረ ሲሆን ፤ ከዚያም በኋላ ኳሱን በቀጥታ ወደ ግብ ቢሞክርም ተከላካዮቹ ተረባርበዉ አዉጥተዋል። በ77ተኛዉ ደቂቃ ላይም ከግራ መስመር በኩል የተሻገረዉን የቅጣት ምት ኳስ ተከላካዩ ፍሬዘር ካሳ በቀጥታ ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ወደ ዉጭ ወጥታለች።
የጨዋታዉ ደቂቃ እየገፋ በሄደ ቁጥር ሁለቱም ክለቦች ጫና ፈጥረዉ በመጫወት አደጋዎችን ለመፍጠር እና ጎሎችን ለመፍጠር ሲያደርጉ የነበረዉ ጥረት ሳይሳካ ቀርቶ ጨዋታዉ ያለ ግብ 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት ተጠናቋል።