By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: መቻል የሊጉን መሪነት ሲረከብ ፤ ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !!
Share
Notification Show More
Latest News
ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ወልዋሎ ዜናዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡና የጨዋታ ዘገባ መቻል
ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ
ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ኢትዮጵያ ቡናወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባፋሲል ከነማመቻልየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

መቻል የሊጉን መሪነት ሲረከብ ፤ ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !!

Ermias Misganaw
Ermias Misganaw 2 years ago
Share
SHARE

* በአስራ ዘጠነኛው ሳምንት የመጀመሪያ መርሐግብር መቻል በምንይሉ ወንድሙ ብቸኛ ግብ ወላይታ ዲቻን 1ለ0 በሆነ ዉጤት ማሸነፍ ችሏል።

በትላንትናው ዕለት በድንገት ህይወቱ ላለፈዉ የባህርዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አለልኝ አዘነ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘዉ መሪነት ቀን አስር ሰዓት ሲል በጀመረዉ ጨዋታ በወቅቱ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ሜዳዉ ያን ያህል በምቾት ኳስ ለመጫወት አመቺ ስላልነበረ ሁለቱም ክለቦች ይህ ነዉ የሚባል ተጠቃሽ ሙከራ እምብዛም ሊያስመለክቱን አልቻሉም ።

በዚህ ሂደት መከናወን በቀጠለዉ ጨዋታ በግማሽ ሰዓት ላይ መቻሎች መሪ መሆን የቻሉበትን ግብ አግኝተዋል ። በዚህም ከኋላ ክፍል የተጣለዉን ኳስ ሽመልስ በቀለ ተቆጣጥሮ ሳጥን ውስጥ በመግባት ለምንይሉ ሲያቀብለዉ አጥቂዉ ኳሷን ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል።

- ማሰታውቂያ -

እረፍት በፊት ከነበረዉ በተወሰነ መልኩ ሙከራዎችን ባስመለከተን ሁለተኛዉ አጋማሽም መሪዎቹ መቻሎች በሽመልስ በቀለ እና በግብ አስቆጣሪዉ ምንይሉ ወንድሙ አማካኝነት ሙከራዎችን ማድረግ ችለዉ የነበረ ቢሆንም የግብ ዘቡ ቢኒያም ገነቱ ሙከራዎቹን ተቆጣጥሯል።

በ63ተኛዉ ደቂቃ ላይ ዳግም ጥሩ የግብ ዕድል አግኝተዉ በምንይሉ አማካኝነት ሙከራ ማድረግ ችለዉ የነበሩት መቻሎች በይበልጥ በኳስ ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርገዉ ለመንቀሳቀስ ሲሞክሩ ተስተውሏል። በተደጋጋሚ በሚጥሏቸዉ ረጃጅም ኳሶች አንዳች ነገርን ለመፍጠር ሲጥሩ የነበሩት ዲቻዎች በ72ተኛዉ ደቂቃ ላይ በአበባየሁ አጂሶ አማካኝነት ሙከራ ቢያደርጉም ግብ ጠባቂዉ ኤልዌንዚ ተቆጣጥሯታል።

በሁሉም ረገድ የተቀዛቀዘ የጨዋታ እንቅስቃሴ ባስመለከተን የቀኑ ጨዋታም በመጨረሻው ደቂቃ ላይ ወላይታ ዲቻ በእዮብ ተስፋየ አማካኝነት አስደናቂ ሙከራ አድርገዉ የነበረ ቢሆንም ኳሷ የግቡን ቋሚ ነክታ ወደ ዉጭ ወጥታለች ፤ በዚህም የሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ 19ነኛ ሳምንት ጨዋታ በመቻል 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

* በምሽቱ ሁለተኛ መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና እና ፉሲል ከነማ መርሐግብራቸዉን በአቻ ዉጤት አገባደዋል።

በኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ በላይ ታደሰ መሪነት ምሽት ላይ በጀመረዉ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ሁለቱም ክለቦች ተመጣጣኝ የሚባል የጨዋታ እንቅሰቃሴ ያስመለከቱን ሲሆን ፤ ክፍት በነበረዉ ጨዋታም በሁለቱም በኩል ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ለመመልከት ችለናል።

በዚህም በ15ተኛዉ ደቂቃ ላይ የመጀመሪያ ሙከራ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ከግራ በኩል ከአቤል እንዳለ የተቀበለዉን ወደ ግብ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ ግን በአናት ላይ ወጥታለች። በዚህ ሂደት ጅማሮዉን ባደረገዉ መርሐግብሩ በ20ኛዉ ደቂቃ ላይ የግብ ዘቡ በረከት አማረ እና አማኑኤል ገ/ሚካኤል እርስ በእርስ ተጋጭተዉ ጉዳት አጋጥሟቸዉ ከሜዳ ወጥተዋል።

በሂደት እየተጋጋለ በቀጠለዉ ጨዋታ ቡናማዎቹ በበፍቃዱ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ከሳጥን ውጭ አድርገዉ የነበረ ቢሆኖንም ኳሷ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወጥታለች። በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም በ31ኛዉ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ የገባዉ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ ያቀበለዉን ኳስ አቤል እንዳለ በቀላሉ ወደ ግብነት ቀይሮ አፄዎቹን መሪ አድርጓል።

ከግቧ መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ሲጥሩ የተስተዋሉት ቡናማዎቹ አብዱል ከሪም ያቆመለትን ኳስ መስፍን በቀጥታ ወደ ግብ ሲመታ ሳማኪ በድንቅ ብቃት ሲመልስ ዳግም የተገኘዉን ኳስ በፍቃዱ ሞክሮ የነበረ ቢሆንም ኳሷ በግቡ ቋሚ ለጥቂት ወጥታለች።

በዚህ ሂደት በቀጠለዉ ጨዋታም አጋማሹ ሊጠናቀቅ ሲል መስፍን ታፈሰ ከአብዱል ከሪም የተቀበለዉን ኳስ ከተከላካዮች ጋር ታግሎ ወደ ግብነት በመቀየር ክለቡን አቻ አድርጎ አጋማሹ ተጠናቋል። በሁለተኛዉ አጋማሽ በመጠኑም ቢሆን ብልጫ የተወሰደባቸዉ ቡናማዎቹ በ58ተኛዉ ደቂቃ ላይ በአብዱልከሪም አማካኝነት እና ከአንድ ደቂቃ በኋላ ደግሞ መስፍን ታፈሰ ከዚሁ ተጫዋች በተቀበለዉ ኳስ ድንቅ ሙከራ ማድረግ ችለዋል።

በጥሩ ፉክክር በቀጠለዉ ጨዋታ በ78ተኛዉ ደቂቃ ላይ ዳግም ቡናማዎቹ በተከላካዩ ዋሳዋ ጂኦፍሪ አማካኝነት ከርቀት ድንቅ ሙከራ ቢያደርጉም የግብ ዘቡ ሳማኪ ኳሷን አውጥቷታል። በተደጋጋሚ በግራ በኩል በኢትዮጵያ ቡናዉ የመስመር አጥቂ መስፍን ታፈሰ እንቅስቃሴ ተቸግረዉ የነበሩት እና እየተቀዛቀዙ የሄዱት አፄዎቹ በጨዋታው መገባደጃ ወቅት በ83ተኛዉ ደቂቃ ላይ በሽመክት ጉግሳ አማካኝነት ድንቅ ሙከራ ቢያደርጉም ኳሷ የግቡን ቋሚ ነክታ ወደ ዉጭ ወጥታለች። የሳምንቱ ታላቅ መርሐግብርም አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ተጠናቋል።

You Might Also Like

ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ አሸንፏል

ኢትዮጵያ ቡና የፋይናስ ችግር እንገጠመው ተገለፀ

“ኢትዮዽያ ቡናን ብትነኩ ከመቃብሬ ተነስቼ አጠፉቹሀለው” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By Ermias Misganaw
Follow:
Writer at Hatricksport
Previous Article የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰባዊ ሩጫ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተባለ
Next Article የኢትዮጵያ ቡና የቤተሰብ ሩጫ የ2 ሚሊዮን ብር ስፖንሰር አገኘ…

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

የሀድያ ሆሳዕና ክለብ ከተጫዋቾች ክፍያ ጋር በተያያዘ በድጋሚ ችግር ውስጥ ገብቷል

Aku Emati By Aku Emati 4 years ago
​ፖርቹጋላዊው ቫዝ ፒንቶ ቀጣዩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ ሆነው በይፋ ተሾሙ።
“ቅዱስ ጊዮርጊስ የሲቲ ካፑን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ትላልቅ ዋንጫዎች ጠራርጎ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል” የአብስራ ተስፋዬ (ቅ/ጊዮርጊስ)
በዱባይ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆነዋል
ቅ/ጊዮርጊስ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?