By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰባዊ ሩጫ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተባለ
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎች

የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰባዊ ሩጫ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተባለ

ዮሴፍ ከፈለኝ
ዮሴፍ ከፈለኝ 2 years ago
Share
SHARE

” ምንም መልካም ነገር ብንሰራ ሌቦች መባላችን አይቀርም በኛ በኩል ግን ህግን ተከትለን የደጋፊዎቻችንን ክብር ለመጠበቅ ጥረት አድርገናል”
አቶ ገዛኧኝ ወልዴ
/ የኢትዮጵያ ቡና ዋና ስራ አስኪያጅ/

**…. ከነገ ጀምሮ ሽያጩ ይካሄዳል
**…..ዋጋው 800 ብር ነው ተብሏል

በየአመቱ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ቡና የቤተሰብ ሩጫ “ቡንዬ የኔ” በሚል መሪ ቃል የፊታችን ግንቦት 11/2016 መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ ይካሄዳል።

- ማሰታውቂያ -

በእስካሁኖቹ ስድሰት ቤተሰባዊ ሩጫ ላይ አምስቱ በጎዳና ላይ ሲካሄዱ አንዱ በኮቪድ 19 ምክንያት 30 ሺህ የክለቡ ደጋፊዎች ማሊያ ገዝተው ባሉበት የበጎ አድራጎት ስራ ላይ በመሳተፍ ቀኑን ማሳለፋቸውን የክለቡና የደጋፊ ማህበሩ አመራሮች በሰጡት መግለጫ ላይ አስረድተዋል።

ዛሬ ከቀትር በኋላ በካሌብ ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ላይ የሩጫ ውድድሩ በቀጣዩ ግንቦት 11/2016 የሚካሄድ ሲሆን የቲሸርቱ ዋጋ 800 ብር መሆኑና ከነገ ጀምሮ ሽያጩ በቡና ባንክ ሙሉ ቅርንጫፎች፣ በክለቡና በደጋፊ ማህበሩ ጽ/ቤቶች ፣ በክለቡ ስር በታቀፉ 13 ዕድሮችና ክለቡ በመረጣቸው ደጋፊዎች እንደሚከናወን አስረድተው በሚገዙበት ጊዜ ደረሰኙን በትክክል እንዲይዙና ማሊያውን ከወሰዱበት ቦታ ብቻ እንደሚያገኙ አሳስበዋል።

“የቤተሰባዊ ሩጫው ዋና አላማ ክለቡን በገቢ ማጠናከርና የደጋፊውን ቤተሰባዊ ትስስር የተሻለ ማድረግ ነው። ማሊያው የሩጫ ነው የክት እንደምንለው አይደለም አላማው ገንዘብ ማሰባሰብ መሆኑን መታወቅ አለበት በሩጫውም 35 ሺህ ሰው ይገኛል ብለን እንጠብቃለን”
ያሉት ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ገዛኧኝ ወልዴ እንደገለጹት ” ምንም መልካም ነገር ብንሰራ ሌቦች መባላችን አይቀርም በኛ በኩል ግን ህግን ተከትለን የደጋፊዎቻችንን ክብር ለመጠበቅ ጥረት አድርገናል” ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። አቶ ገዛኧኝ ክለባችን ከሌሎች ክለቦች የሚለየው የፋይናንስ ምንጩ ህዝቡ መሆኑ ነው ለዚህ ነው ክለቡ ህዝባዊ ነው የምንለው ” ሲሉም አስተያየት ሰጥተዋል።

የደጋፊ ማህበሩ አመራር የሆኑት አቶ ሰለሞን ታምራት
የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ የሩጫ ውድድሩን በደንብ ጓጉቶ እንደሚጠብቀው አውቃለሁ ደጋፊያችን ማን እንደሆነ የሚያሳይበት ውድድር በመሆኑ የተነሳንበት አላማ እንደሚሳካ እምነቱ አለኝ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

ኬ ሀውሲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሩጫ ውድድሩ የፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር መሆኑም ይፋ ተደርጓል። የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ወሰንሰገድ አሰፋ “የዚህን ተወዳጅና የበርካታ ደጋፊ ባለቤት የሆነውን ኢትዮጵያ ቡናን ስፖንሰር በመሆናችን ትልቅ ኩራት ተሰምቶናል ድርጅታችን በ10 አመት ውስጥ 100ሺህ ኢትዮጵያዊያንን የቤት ባለቤት ለማድረግ አቅዶ የተመሰረተ ነው በዚህ ሰአት የመጀመሪያው ዙር ቤት ለደረሳቸው እድለኞች ርክክብ እያደረግን ነው አዋጭና አስተማማኝ በመሆኑ ትልቅ ስኬት ያለው ስራ እንሰራለን ብለን እናምናለን ለውድድሩም ስኬት መልካም እድል እንላለን” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በዚህ የክለቡ የቤተሰባዊ የሩጫ ውድድር ላይ ከኬ ሀውሲንግ ውጪ ሀበሻ ቢራ፣ ቡና ባንክ፣ ቤቲካ፣ና ከሀ እስከ ፐ የተሰኙት ተቋማትም በአጋርነት ድጋፍ ማድረጋቸውን በመግለጽ አመራሮቹ አመስግነዋል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
By ዮሴፍ ከፈለኝ
Follow:
Editor at Hatricksport
Previous Article የአዲስ አበባ ስታዲየም ለተመልካች ዝግ መሆኑ ተነገረ….
Next Article መቻል የሊጉን መሪነት ሲረከብ ፤ ኢትዮጵያ ቡና እና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል !!

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
ወላይታ ድቻዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስየጨዋታ ዘገባቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ

የጨዋታ ዘገባ | ፈረሰኞቹ በሄኖክ አዱኛ ብቸኛ ግብ ከጦና ንቦቹ ሶስት ነጥብ ወስደዋል

Habtamu Mitku By Habtamu Mitku 4 years ago
​የክብር ጨዋታውን  በማሸነፋችን ደስተኞች ነን |አቅሌስያስ ግርማ
“ለኢትዮጵያ ቡና ያስቆጠርኩት ጎል በሊጉ የመጀመሪያዬ ስለሆነች ለየት ያለ ደስታ ተሰምቶኛል” ሚኪያስ መኮንን (ኢትዮጵያ ቡና)
ሪፖርት | አቤል አሰበ በጭማሪ ደቂቃ ጎል ለድሬዳዋ ጣፋጭ ሦስት ነጥብ አስገኝቷል
በአፍሪካ ዋንጫው ዝቅተኛ ግምት እንደሚሰጠን ብናውቅም ወደ ውድደሩ ስፍራ የምናመራው አንድ ደረጃ ከፍ ለማለትና ክስተት ለመሆን ነው” የዋልያዎቹ ረዳት ካፒቴን አስቻለው ታመነ
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?